በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የሲቲእስካን እና ራጅ ክፍል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የሲቲእስካን እና ራጅ ክፍል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ  ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፤የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ TIN/ ያላቸው።
  2. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 50 በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዘውትር በስራ ቀንና ሰዓት ለሰነድ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 300/ሶስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ኮፒ በማድረግ በታሽገ ኤንቨሎፕ በአብክመ ከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስተኛው/16 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 4፡01 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ይታሽጓል።
  4. ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ እለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% / ከሁለት ፐርሰንት/በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ትእዛዝ/CPO/ማስያዝ አለባቸው።
  6. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ግዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. የስራው ቦታ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ይሆናል።
  9. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን።
  10. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 0972847872 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

በአብክመ ጤና ቢሮ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-08
  • Bid closing time: 10:01
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ቀን ከጠዋቱ 4፡01 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-08 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Kemise General Hospital
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jul 24, 2026
  • Posted at: 2026-07-24T09:48:35.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders