Chemicals and Reagents
በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ልዩ ልዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፈ/ህ/አጠ/ስፔ/ሆ_003/12
በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተገለፁትን
- ምድብ 1. መድሃኒት ሪኤጀንትና ሳፕላይስ ግዥ
- ምድብ 2 የፅህፈት መሳሪያዎች
- ምድብ 3 የመኪና ጎማ ፣ ዘይትና ቅባት ግዥ
- ምድብ 4 የህክምና መሳሪያ ስፔር ፓርት
- ምድብ 5 የካርድ ክፍል ሸልፍ
- ምድብ 6 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ ማንኛውንም የመንግስት ግብርና ታክስ ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ውል በመያዝ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶችን አሟልታችሁ በጨረታው መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይነት መለያ /TIN CARD ሰርቲፊኬት ያላቸው እና በግብር ዓመቱተገቢውን የታክስና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና በመንግስት ግዥ አቅራቢነት EJP የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
3. አጠቃላይ የገንዘቡ መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተቁ 1- 3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘ ማቅረብ አለባቸው።
5. አጠቃላይ ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።
6. ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 500.00/ አምስት መቶ ብር/ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሆስፒታሉ ማግኘት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማንኛውንም ግብር ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ
- ለምድብ 1 መድሃኒት ሪኤጀንትና ሳፕላይስ 150000.00 / አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/
- ምድብ 2 የፅህፈት መሳሪያዎች 10000.00 /አስር ሺህ ብር/
- ምድብ 3 የመኪና ጎማ ዘይትና ቅባት ግዥ 50000.00/ ሃምሳ ሺህ ብር/
- ምድብ 4 የህክምና መሳሪያ ስፔር ፓርት ግዥ 20000.00 /ሃያ ሺህ ብር/
- ምድብ 5 የካርድ ክፍል ሸልፍ 10000 /አስር ሺህ ብር/
- ምድብ 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ 10000.00 /አስር ሺህ ብር/ ግዥ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅጽ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት 8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡15 ይታሸጋል።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። ቀኑ በዓል /ዝግ/ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 57 38 /0222 09 16 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል /ባህር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-09-28
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-28 14:15
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት 8:15 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Felegehiwot General Specialized Hospital
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T08:11:48.000Z
- Source: 2merkato