Stationery
የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2019
የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት በጨረታ ቁጥር አየ/አ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት 01/2019 መሰረት የ2019 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ግዢ መለያ ቁጥር አየ/አ/2ኛ/ደረጃ ት/ቤት 01/2019
|
ተ ቁ
|
የእቃውና አገልግሎቱ አይነት
|
የግዥ ሎት ምድብ |
የግዥው ምድብ |
የጨረታው ማስከበሪያ የብር መጠን |
|
|
1 |
የአላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
|
ሎት 1 |
እቃ |
10,000
|
00 |
|
2 |
የደንብ ልብስ
|
ሎት2 |
እቃ |
10,000
|
00 |
|
3 |
የፅዳት እቃዎች
|
ሎት3 |
እቃ |
15,000
|
00 |
|
4 |
የፈርኒቸር እቃዎች
|
ሎት4 |
እቃ |
10,000
|
00 |
|
5 |
የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ እቃዎች
|
ሎት5 |
እቃ |
15,000
|
00 |
|
6 |
የህንፃ መሳሪያ እቃዎች
|
ሎት6 |
እቃ |
10,000
|
00 |
|
7 |
የስፖርት እቃዎች
|
ሎት7 |
እቃ |
10,000
|
00 |
|
8 |
ህትመት
|
ሎት8 |
አገልግሎት |
6,000
|
00 |
|
9 |
የደንብ ልብስ ስፌት
|
ሎት9 |
አገልግሎት |
5,000
|
00 |
|
10 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና
|
ሎት10 |
አገልግሎት |
4,000
|
00 |
|
11 |
መፅሃፎችና የትምህርት መረጃ መሳሪያዎች |
ሎት11 |
እቃ |
8,000
|
00 |
|
12 |
የፍሳሽ ማስወገድ/ ሽንት ቤት ማስመጠጥ/
|
ሎት12 |
አገልግሎት |
3,000
|
00 |
|
13 |
የውሃ መስመሮች ጥገና
|
ሎት13 |
አገልግሎት |
3,000
|
00 |
|
14 |
የፈርኒቸር እቃዎች ጥገና
|
ሎት14 |
አገልግሎት |
3,000
|
00 |
|
15 |
የትራንስፖርት አገልግሎት
|
ሎት15 |
አገልግሎት |
3,000
|
00 |
|
16 |
ኬሚካሎችና የላብራቶሪ የትምህርት መሳሪዎች |
ሎት 16 |
እቃ |
10,000
|
00 |
ከሎት ቁጥር 8 – 15 የተጠቀሱት የአገልግሎት ግዢዎች በበጀት ዓመቱ አገልግሎቱ በሚፈለግበት ወቅት በሚታዘዘው መጠን ልክ ሲሆን ውሉ ጸንቶ የሚቆየው እስከ በጀት አመቱ መዝጊያ መሆኑን እናሳውቃለን።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና በ2018ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን
ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው።
3. ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜያቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ ከላይ በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። CPO ሲዘጋጅ በአየር አምባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስም መሆኑን እንገልፃለን።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለማስገባት በሚመጣበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አብሮ ማስገባት አለበት ሳምፕል ለማቅረብ ምቹ ያልሆኑ እቃዎችን በፎቶ ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማናወዳድር መሆኑን በቅድሚያ ት/ቤቱ ይገልጻል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እንዲሁም CPO ከኮፒው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ እና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በማግስቱ ማለትም በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫትን ያካተተ መሆኑ መገለጽ አለበት።
8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
9. ት/ቤቱ አሸናፊው ተጫራች ያቀረበው ዋጋ ሳይቀየር 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ ይኖርበታል።
11. ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
13. ለሎት 15 የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ 2% ተመዝጋቢ የሆነ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል።
አድራሻ፡- በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ቦሌ ሚካኤል ሩዋንዳ ኤምባሲ ጀርባ 500ሜትር ገባ ብሎ ለበለጠ መረጃ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር፡- 011-822 0132 / 011-822 0137 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30
- Bid opening: 2026-10-01 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ayer Amba Secondary School
- Buyer address: ቦሌ ሚካኤል ሩዋንዳ ኤምባሲ ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T07:24:02.000Z
- Source: 2merkato