Stationery
የናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት የስቴሽነሪ እና የቢሮ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ NCO/0457/2026
የጽህፈት መሳሪያ ግዢ
የናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት በ“CADiR” (Collective Action for Disability Rights) ፕሮጀክት አማካኝነት ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ወጣቶች ትምህርታዊ ድጋፍ እና ለድርጅቱ ቢሮ ስራዎች የሚውሉ የስቴሽነሪ እና የቢሮ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ስለ ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት (NCO)
ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት (NCO) በሚያዚያ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. (License No. 6792) የተመዘገበ ሀገር በቀል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ በአእምሮ ጤና፣ በማህበራዊ ድጋፍ (psychosocial support) እና አካል ጉዳተኞችን በማካተት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። NCO ከመንግስት ተቋማት፣ ከትምህርትና ጤና ዘርፎች፣ ከሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት (OPDs) ጋር በትብብር ይሰራል።
2. የሚፈለጉ ቁሳቁሶች ምድብ (Procurement Category / Lot)
- Stationery & Office Supplies (የጽህፈት መሳሪያ ግዢ)
3. የጨረታው ተሳታፊዎች ማሟላት የሚገባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ: በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ TIN እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑበት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የብራንድና ቴክኒክ መግለጫ (Brand & Specifications): ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው እቃዎች በሙሉ ብራንድ (Brand)፣ የአምራች ስም (Manufacturer) እና ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ (Market Specific Specification) በግልጽ ማመልከት አለባቸው።
- የትራንስፖርትና ማጓጓዣ አገልግሎት ዲክላሬሽን: አቅራቢዎች ዕቃዎቹን እስከ ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት (አዲስ አበባ) ድረስ የማጓጓዝ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን ወይም የማይሰጡ መሆኑን በፋይናንሻል ፕሮፖዛላቸው ላይበግልጽ መጥቀስ አለባቸው።
- የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት (Mandatory Price Quotation Format): ተጫራቾች በተሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት (Quantity Offered = 1) በመጠቀም የአንድ ዕቃ አጠቃላይ የገበያ ዋጋ ተመን (Price of One Unit) ማቅረብ አለባቸው።
- የማስረከቢያ ጊዜና ዋስትና: የአቅርቦት ጊዜ ሰሌዳ እና አስፈላጊ ለሆኑ እቃዎች ጥራትና ዋስትና ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
4. የጨረታ ማስገቢያና መክፈቻ ጊዜ ሰሌዳ
- የጨረታው ማስታወቂያ የሚወጣበት ቀን: ቅዳሜ፣ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. / September 19, 2026
- የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን፡ ቅዳሜ ፣ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. / Saturday, October 03, 2026 ከቀኑ 11:00 ሰዓት በፊት።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን፡ ማክሰኞ ፣ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. / Tuesday, October 06, 2026 ከቀኑ 4:30 ሰዓት ላይ።
አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛልን) በሁለት የተለያዩ ኢንቭሎፖች ታሽገው በተፈረሙ ፖስታዎች በማድረግ፣ በአጠቃላይ በሶስተኛ ጥቅል ፖስታ ውስጥ በማሸግ በናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 በአድራሻችን በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ: ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት
ስልክ፡ 0993252797 / 0945482424
ኢሜይል: [email protected] , [email protected]
አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02
Tender details
- Deadline: 2026-10-03
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-10-06 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Natanim Charitable Organization (NCO)
- Buyer TIN: 0084298990
- Published on: 2merkato.com (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T09:19:34.000Z
- Buyer website: https://natanimethiopia.org/
- Source: 2merkato