Stationery

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

ሎት

የግዥው አይነት

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን

1

ሎት 1

አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች ግዥ

01/2019

12500.00

2

ሎት 2

የጽዳት ዕቃዎች

"

12500.00

3

ሎት 3

የህትመት ሥራዎች

"

10000.00

4

ሎት 4

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

"

21000.00

5

ሎት 5

የደንብ ልብስ

"

12500.00

6

ሎት 6

ቋሚ ዕቃዎች

"

15000.00

7

ሎት 7

የሕክምና ዕቃዎች

"

57000.00

8

ሎት 8

የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች

"

40000.00

በመንግሥት ግዥና ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውንና ቫት ከፋይ የሆኑ ፐIN Number ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ QR-Code ደረሰኝ ያለው መሆን አለበት።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎቱ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 የማይመለስ ብር 200.00 /ብር ሁለት መቶ /በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውንና ማንዋሉን በታሸገ ፖስታ በ2 ኮፒ በማድረግ ከ2፡30 -11፡00 ሰዓት ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  5. ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ፎቶ ኮፒውን በአንድ ፖስታ፣ ዋናውን በአንድ ፖስታ ተደርጎ ፖስታው ላይ ዋና ወይም ፎቶ ኮፒ ተብሎ ይገለጽ።
  7. ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጐ በዚያኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ከ11ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ማለትም ሰኞ ይከፈታል።
  8. ከወጣው ጨረታ ብዛት ላይ መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር 20 በመቶ የመቀነስ መብት አለው።
  9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊ ተጫራቾች ባመጣው ናሙና መሰረት ዕቃውን ማቅረብ ይጠበቅበታል። ቋሚ ዕቃዎችን መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ይኖርበታል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው።
  11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በቀረበው ሎት መሠረት ፖስታ ላይ መገለጽ ይኖርበታል።
  12. ተጫራቾች ለአሸነፉበት ዕቃ ዋጋ 10% CPO ማስያዝ አለባቸው።
  13. በራሳቸው ትራንስፖርት የጨረታ አሸናፊ ድርጅት መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  14. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሠረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
  15. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳችሁን ዋናውንና ኮፒ ሰነድ ልትገዙ ስትሉ ማቅረብ አለባችሁ።
  16. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ እና እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

አድራሻ፡- ከኢምፔሪያል 100 ሜትር ገባ ብሎ ሳሚ ሕንፃ ፊት ለፊት ኬቢ የአሽከርካሪ ማሠልጠኛ ጀርባ መሆኑን እንገልጻለን።

የቢሮ ስልክ .ቁ 011 8 22 99 52

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳዳር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-01
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-01 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole 17 Health Post
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
  • Posted at: 2026-09-19T08:34:08.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders