Food and Beverage

የደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ/ ደሴ ማረሚያ ቤት/ በስሩ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል እና የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ/ ደሴ ማረሚያ ቤት/ በስሩ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል፡-

  1. የምግብ እህል፡- ቀይ ማሽላ፣ ነጭ ማሽላ፣ ባቄላ ክክ፣ አተር ክክ፣ ተቆልቶ የተከካ የሽሮ ባቄላ፣ ተቆልቶ የተከካ የሽሮ ጓያ፣ በቆሎ
  2. ዛላ በርበሬ፣ የዳቦ ፍርኖ ዱቄት
  3. ቅመማ ቅመም፣ የወጥ የፈረንጅ ቀይ ሽንኩርት፣ ዝቃቅቤ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ ነጭ አዝሙድ እና የመሳሰሉት፣
  4. ሸቀጣ ሸቀጥ፣ የልብስ ሣሙና፣ የእቃ ማጠቢያ ሣሙና አጃክስ/ ፣ መኮረኒ፣ ፓስታ፣ ሩዝ፣ የዕቃ ማጠቢያ ሽቦና የመሳሰሉት፡-
  5. ደረቅ የማገዶ የባህር ዛፍ እንጨት / ከመስከረም 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ማቅረብ የሚችሉ ነጋዴዎችን እንደየ ሁኔታው ለአንድ ዓመት በማጫረት ከአሸናፊው ጋር ውል ለመያዝ ይፈልጋል።
  6. የጽሕፈት መሣሪያ፣ ቋሚ እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ አላቂ እቃ፣ የሕትመት፣ የሕንፃ መሣሪያ

ስለዚህ ፡-

1. ለሁሉም የሥራ ዓይነት በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ለሁሉም የሥራ ዓይነት በየዘርፉ የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት የሚጫረቱበትን የእህል ዓይነትና ዛላ በርበሬ ናሙና ከ50 ግራም ያላነሰ ይዞ መቅረብ አለበት። ናሙና ማቅረብ ያልቻለ ተጫራች በጨረታው መጫረት አይችልም።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ብዛት የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር ብር በአንድ ዓመት አባዝተው የእዚያን 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በአማርኛ የተተረጐመ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በጥሬ ገንዘብ በመሂ/ ማስያዝ ይኖርበታል።

5. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ የሁሉም የሥራ ዘርፍ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ከደሴ ማረ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ከፍሎ መውሰድ ይችላል።

6. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሰነድ የሚገዛበት ሆኖ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በደቡብ ወሎ ደሴ ማረሚያ ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከረፋዱ 4፡30 ታሽጐ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀናት ከረፋዱ 4፡30 ታሽጐ 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

8. የጨረታው አሸናፊ በአሸነፉት መሰረት ውል ባይወስዱ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል። አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ያሸነፉበትን ዕቃ ማረ/ቤቱ ድረስ በራሱ ወጭ ያስረክባል።

9. አንዱ ባቀረበው የጨረታ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ሌላው ማቅረብ የለበትም።

10. አቅርቦቱን በተመለከተ ከወጥ ሽንኩርት በስተቀር ማረ/ቤቱ በሚፈልገው መጠንና ልክ መሰረት ወር ከመግባቱ በፊት ከ25-30 ቀን ድረስ የወሩን የምግብ ፍጆታ እና የማገዶእንጨት አጠቃሎ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

11. የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% የአንድ ዓመት ጠቅላላ ዋጋ የሚያሲይዝ ሲሆን ተጫራቾች ማብራሪያ የፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0331116516 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።

12. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ለሚያደርጉት ግብይት ሕጋዊ የሆነ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለበት።

13. ለታራሚዎች በአማካይ በየወሩ የሚቀርብ የምግብ እህል፣ ቅመማ ቅመም፣ የማገዶ እንጨት ወዘተ… ብዛት በአማካይ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለጽ ይሆናል።

14. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-01 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: South Wello Prisons Directorate
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
  • Posted at: 2026-09-19T07:57:38.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders