Equipment and Accessories

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር- 09/2019 የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሸያጭ

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ/ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታዉን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያዉ ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳቦችና ቀረጥ ተመላሽ አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት https://t.me/hawassaawegaged  (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018) በሚለው የቴሌግራም ግሩፕ ስሊፕ በመላከ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።

3. ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.PO በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠው የጨረታ ዋስትና(CPO) መጠን ለእያንዳንዱ ኮድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚጀምር ሲሆን ግልጽ ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ የሀራጅ ጨረታ ተሳታፊዎች ምዝገባ ተጀምሮ እንደተጠናቀቀ ይጀምራል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበዉ ዋጋ በሚለዉ ርዕስ ስር በተሰጠዉ ክፍት ቦታ ከነቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።ከዚህ ሰነድ ዉጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።

6. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ስዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ። በተጨማሪ ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠዉን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አልያም አይነበብልኝ ማለት አይችልም።

7. ማንኛዉም ተጫራች የሰጠዉ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታዉ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን, አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።

9. ተጫራቾች የዕቃዉን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።

10. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።

11. አሸናፊዉ ተጫራቾች ማሸነፋውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) የስራ ቀናት ዉስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።

12. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-5396 / 046-212-6595
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-24 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
  • Posted at: 2026-09-19T08:23:31.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders