Uniforms and workwear

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለዲስትሪክታችን ሠራተኞች ለ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ ጫማ፣ የደህንነት መጠበቂያ እና የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለዲስትሪክታችን ሠራተኞች ለ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ጥቅማጥቅም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ኢመአድ ዳ/መ/ጥ/ድ/ቲ 06/2018 ዓ.ም

  • 1. ደንብ ልብስ ጫማ፣ የደህንነት መጠበቂያ እና የፅዳት ዕቃዎች
  • የደንብ ልብስ ሎት 1
  • ጫማ ሎት ፡- 2
  • የደኅንነት መጠበቂያ ሎት፡- 3
  • የፅዳት ዕቃዎች ሎት፡-4

ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000322267979 ገቢ በማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡።
  • በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ አለባቸው
  • በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በመንግሥት የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በኤጀንሲው ድረ ገፅ የተመዘገቡበትን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም ሎቶች በድምሩ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክሲፒኦ ወይም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል በዚሁ እለትም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
  • የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ ፡-

  • በቅድመ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና በመ/ቤቱ ናሙና መራጭ ኮሚቴ ታይቶ ተቀባይነት ካገኙት መካከል በዋጋ ዝቅተኛ ሆኖ የተገኘው በአሸናፊነት ይመረጣል።
  • የሚፈለገውን የሠራተኞች ጥቅማጥቅም አይነትና ብዛት በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር መመልከት ይቻላል።
  • ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

ስልክ ቁጥር 025111-13-13/0927636126/0919008017

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ethiopian Roads Administration Dire Dawa Road Maintenance District
  • Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለሁሉም ሎቶች በድምሩ
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
  • Posted at: 2026-07-25T07:07:49.000Z
← Back to all tenders