External audit and assurance

ቪዥን ፎር ኢትዮጵያ አሶሴሽን (Vision for Ethiopia Association) የ2026 እ.ኤ.አ የበጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዱን ብቃት ባላቸው የውጭ ኦዲተሮች አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል

Description

የሂሳብ ምርመራ(ኦዲት) አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ

ቪዥን ፎር ኢትዮጵያ አሶሴሽን (Vision for Ethiopia Association) በምዝገባ ቁጥር 0311 እና በቲን 0005496774 ተመዝግቦ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የበጎ አድራጎት እና የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው። ድርጅታችን የ2026 እ.ኤ.አ የበጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዱን ብቃት ባላቸው የውጭ ኦዲተሮች አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦

 መሠረታዊ የብቃት መስፈርቶች

1. በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተመዘገቡና የታደሰ የኦዲት ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4. የቴክኒካል እና የፋይናንሻል የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የሚችሉ።

የማቅረቢያ ቦታና ጊዜ

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቦሌ ኦሎምፒያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፦ ቦሌ ኦሎምፒያ፣ መሠረተ ክርስቶስ ዋና ቢሮ ሕንፃ፣ 1ኛ ፎቅ (ዴስቲኒ ሆቴል ፊት ለፊት)፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።

ተጨማሪ መረጃ፡-

የጨረታው አሸናፊ ከድርጅቱ ጋር ለ3 (ሦስት) ዓመታት የሚቆይ የሥራ ውል ስምምነት ይፈጽማል። ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፦ 09 11 30 05 60/ 09 10 02 15 02 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

ቪዥን ፎር ኢትዮጵያ አሶሴሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-01
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-08-01 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Vision For Ethiopia Association
  • Buyer address: Bole Olympia behind of Deluxe furniture passing through Admas University and beside of Destiny Hotel MKC building 2nd floor
  • Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
  • Posted at: 2026-07-25T07:19:56.000Z
← Back to all tenders