Electrical installation and wiring
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለፌደራል ገቢዎች ባ/ዳር ቅርንጫፍ ግንባታ ፕሮጀክት የተለያዩ ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ድጋሜ የወጣ ግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር 01/1019 እና 20/2019
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ይዞ ለሚገነባቸው፡-
1. ለፌደራል ገቢዎች ባ/ዳር ቅርንጫፍ ግንባታ ፕሮጀክት የTempered Glass Work አቅርቦት እና ገጠማ ስራ በጨረታ ቁጥር 01/2018
2. ለፌደራል ገቢዎች ባ/ዳር ቅርንጫፍ ግንባታ ፕሮጀክት፣ ለደሴ አሚኮ ግንባታ ፕሮጀክት የዳታ፣ ቴሌ፣ ቲቪ፣ ሲሲቲቪ፣ ኦዲዮ፣ ፋየር አላርም ሲስተም፣ መብረቅ መከላከያ፣ ፍሎር ቦክስ፣ ኬብል ትሪና ላደር፣ ባዝ ወይ እና ሌሎች እና ለጎንደር ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ፕሮጀክት Traffic Barriers አቅርቦት እና ገጠማ ስራ በጨረታ ቁጥር 02 /2019 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ ፈቃድ ለማደስ ግብር ስለመክፈላቸው የሚሰጥ ማስረጃ ያለው/ያላት፤ ለተጠቀሱት ለሁሉም ስራዎች አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ከዚህ በፊት ለመስራታቸው ህጋዊ ከሆነ ተቋም የመልካም ስራ አፈጻጸም ማስረጃ አና ለዚሁ ማስረጃ በአስረጅነት የሚያገለግሉ መረጃዎችን አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም /unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
3. የጨረታ ሰነዱ ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11ባ እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውስድ ይችላሉ፤
4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ባ/ዳር ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል። 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ጨረታው የሚከፈተው ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 የግን ግብ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ ክፍል ነው።
5. ውድድሩ በሎት በጥቅል/ ዋጋ የሚታይ ይሆናል፤ ዝርዝር የጨረታ መመሪያው እና የውል ይዘቱ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው።
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ባ/ዳር 058-218-05-38/09-18-01-06-17/0913-27-60 57/09-18-71-66-16 አዲስ አበባ፡- 011-126-56-52/5145/09-12-08-56-39
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-08-08
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-08 14:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
- Posted at: 2026-07-25T07:33:36.000Z