Oromia
የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ ምግብ እና መጠጥ ከነመስተንግዶው፣ ሻይ ቡና አገልግሎት እና የመኝታ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ ምግብ እና መጠጥ ከነመስተንግዶው፤ ሻይ ቡና አገልግሎት፤ የመኝታ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን።
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበት ተጓዳኝ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸል።
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ብር ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
5. አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ መ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል።
6. አቅራቢው ድርጅት ያሸነፈባቸውን አገልግሎት ወጪ በመቻል በተፈለገበት ቦታ መ/ቤቱ ክፍል ድረስ በማምጣት አገልግሎት መስጠት ይኖርበታል።
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል የጨረታ ሰነድን መውሰድ ይችላሉ።
8. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል። 9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0934866474/0913313780 ደውለው ይጠይቁ።
የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-12 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Bale Zone Robe City Administration FEDB
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ብር
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
- Posted at: 2026-07-25T07:45:26.000Z