Uniforms and workwear
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ.የተ.የግል ማህበር የደንብ ልብስ የሚሰፋ ብትን ጨርቅ ካኪ ቴትረን 6000፣ ካኪ ጨርቅ፣ የተዘጋጁ የወንድና የሴት ሸሚዞች፣ የወንድና የሴት ጫማዎች፣ የዝናብ ልብስ እና ዣንጥላ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ሰነድ ቁጥር 005/2018
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የደንብ ልብስ የሚሰፋ ብትን ጨርቅ ካኪ ቴትረን 6000፣ ካኪ ጨርቅ፣ የተዘጋጁ የወንድና የሴት ሸሚዞች፣ የወንድና የሴት ጫማዎች፣ የዝናብ ልብስ፣ ዣንጥላ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እየገለጽን፡-
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ህጋዊ አካል የተፃፈ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ፣ ምዝገባ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት በሚገኘው መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛው ፎቅ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ፋይናንስ ግዥ ንብረት አስተዳደር መምሪያ መግዛት ይችላሉ።
4. ማንኛውም ተጫራች ብር 50,000.00 (ሀምሣ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ /CPO/ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርቸዋል።
5. አሸናፊው ድርጅት በአምስት ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት መፈረም አለበት።
6. የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
8. ጨረታው ኢአ መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንፃ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/ የተ/የግ/ማህበር ፋይ/ግዢ/ንብ/አስ/መምሪያ 7ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል።
9. ለጨረታ በሚመጡበት ወቅት ሳምፕል ናሙና እና ዋጋውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ የውል ማስከበሪያ የአሽነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ከድርጅቱ ጋር ውል በመግባት ወደ ስራው ይገባል።
11. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
12. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል።
13. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
- ስልክ ቁጥር 011 552 10 09 /011 552 14 58 ፖ.ሣ.ቁ 9515 ፋክስ 011 551 3654
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-10
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-10 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Wendo Trade and Investment Company
- Buyer address: መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
- Posted at: 2026-07-25T07:51:04.000Z