Disposal, scrap and surplus sales

ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ. የእርሻ ማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች የፐርኪንስ መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ የእርሻ ማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች የፐርኪንስ መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተዘረዘሩት የተለያዩ የማሴ ፈርጉሰን እና የፐርኪንስ መለዋወጫ ዕቃዎች አጠቃላይ መመሪያዎች እና ግዴታዎች

1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ደንበኞች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ በጨረታ ሰነድ ቅፅ ላይ በመሙላትና ለጨረታ ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በሲፒኦ ብቻ በማስያዝ በሳሪስ ቶታል አቅራቢያ በሚገኘው የኩባንያው የእርሻ ማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ንዑስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

3. በዚህ የግዥ ጨረታ የሚቀርቡ ሰነዶች በሙሉ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ መፃፍ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች ለመግዛት የወሰነበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ለእያንዳንዱ መለዋወጫ ዕቃ መለያ ቁጥር በተናጥል መጥቀስ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚፈልጉትን የመለዋወጫ አይነት በመለየት በጥቅል ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ለኩባንያው ገዝብ ተቀባዮች ገቢ በማድረግ ከእርሻ መሳሪያዎች መለዋወጫ ንዑስ የስራ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።

7. ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ዘግይተው የሚቅርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

8. ጨረታ የጨረታ ሰነዱን ማስገቢያ ጊዜ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቸው በተገኙበት ትራንስ ቅርጫፍ በሚገኘው የኩባንያው የስልጠናና የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

9. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ማስታወቂያ ከተገለፀ ቀን አንስቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ ዕሴት ታክስን ጨምሮ ከፍያ መፈፀም ይኖርባቸዋል።

10. በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈፅመው ያሸነፉበትን ዕቃዎች የማያነሱ ከሆነ በእቃዎቹ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ኩባንያው ተጠያቂ አይሆንም።

11. የጨረታ ተሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

12. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 442 1133 / 0911 560 658

ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-08-17
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-18 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ20 ተከታታይ የስራ ቀናት ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ries Engineering S.C.
  • Buyer address: DEBEREZEIT ROAD ADDIS ABABA
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
  • Posted at: 2026-07-25T08:08:53.000Z
← Back to all tenders