Disposal, scrap and surplus sales

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃው አይነት

መለኪያ

የጨረታ ማስከበሪያ

1

ያገለገሉ የኮምፒውተር ዩፒኤስ ከነባትሪው (used uPs with batteries)

በቁጥር

200,000.00

2

ያገለገሉ የአውሮፕላን ነዳጅ (used Defueled Oil )(በርሜሉን ሳይጨምር))

በበርሜል

200,000.00

3

ያገለገሉ የተቃጠለ የሞተር ዘይት (used Burned Motor Oil (በርሜሉን ሳይጨምር))

በበርሜል

200,000.00

4

ያገለገሉ ሃይድሮሊክ እና ስካይድሮል ዘይት (used Hydraulic / Skydroll Oil) (በርሜሉን ሳይጨምር)

በበርሜል

200,000.00

5

ያገለገሉ የምግብ ዘይት (used Edible Oil )(በርሜሉን ሳይጨምር)

በበርሜል

200,000.00

6

ያገለገሉ ከውሃ ጋር የተቀላቀለ የሞተር ዘይት, የሃይድሮሊክ እና ስካይድሮል ድብልቅ ውኃ used Edible Oil,Motor Oil,Hydraulic Skydrol, Defueled Oil Mixed with Water)

በበርሜል

200,000.00

7

ያገለገሉ የአውሮፕላን እና የተሽከርካሪ ባትሪዎች (USED A/C & VEHICLE BATTERIES)

በበርሜል

200,000.00

8

ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት አሉሚኒየም ፎይሎች (used Aluminum Foil)

በቁጥር

100,000.00

9

ያገለገሉ የውኃ መያዣ ፕላስቲኮች (used Plastic Bottles)

በኪሎ

50,000.00

10

ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ከ20-30 ሊትር ጄሪካኖች ክዳን ያለው እና የሌለው (USED PLASTIC JERICAN 20-30 Lt. WITH & WITHOUT Lid)

በቁጥር

 

200,000.00

 

11

ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ጣሳዎች፣ ባልዲዎች ፤ ትንንሽ ጄሪካኖች (5 ሊትር ና በታች (uSED PLASTIC BARRELS TINS, CANS & JERRICANS (5 & BELOW LTRS)

በኪሎ

 

200,000.00

 

12

ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ላፕቶፖች (used Laptop)

በቁጥር

100,000.00

13

ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ታብሌቶች (used Tablet)

በኪሎ

100,000.00

14

ያገለገሉ ፈርኒቸሮች (used Furniture)

በኪሎ

100,000.00

15

ያገለገሉ የቆሻሻ መጣያዎች (used Trash bin 80 Ltr-500 Ltr)

በቁጥር

100,000.00

16

ያገለገሉ የቆሻሻ መጣያዎች (used Trash bin 501 Ltr- 1200 Ltr)

በቁጥር

100,000.00

17

Fluorescent short pin tube 14W with Fixture

በቁጥር

100,000.00

18

LED 40W light with Fixture

በቁጥር

100,000.00

19

ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት የትራስ ሽፋን (used EY- Pillow Case) and አገልግሎት ላይ የዋሉ የጭንቅላት ማስደገፊያ ሽፋን (used EY-headrest cover)

በኪሎ

100,000.00

ማሳሰቢያ

ሀ) በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር WIMNA/C&SAT004/2018 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

ለ) በማናቸውም ግዜ የጨረታ ሰነድ የዋጋ መግለጫ ላይ የሚገለፀው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የታክስ እና ሌሎች ማናቸውንም አይነት አስፈላጊ ክፍያዎችን አያካትትም፤ ማናቸውንም የቫት፤ የታክስ እና ሌሎች አስፈላጊ ክፍያዎችን በሙሉ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፤

ሐ)ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኦሪጅናል (Deposit slip) በመያዝ የጨረታ ሠነዱን ነሀሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም እና ነሀሴ 5 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡30 እንዲሁም 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት 8፡00 እስከ 10:00 ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት መግቢያ በር ድረስ ትኬት ቢሮ በር አጠገብ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

መ) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና ነሀሴ 7 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:30 እንዲሁም ከሰዓት 8:00 እስከ 10:00 ባለው ግዜ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በቡልቡላ በር በኩል በአካል በመገኘት መመልከት መጎብኘት ይችላሉ።

ሠ) ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ ላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የዕቃዎች አይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ /BlD Bond/ በባንክ የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በቅድሚያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ለጨረታው ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም።

ረ) ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሀሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይሆናል የጨረታው አሸናፊም በዚሁ ሰዓት ተጫራቾች ባሉበት ወዲያውኑ ተለይቶ ይታወቃል፡፡ ተጫራቾች በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 4፡30 ሠነዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠገብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond) የሚገዙበትን ዋጋ ከሞሉበት የጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

ሰ) በትክክል የማይነበብ ፣ያልታሸገ ፖስታ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ያለው ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ማሰያዣ (CPO) የሚያስገቡት ሠነድ ውስጥ ካልተካተተ ሠነዱ ውድቅ ይደረጋል።

ሸ) ከተራ ቁጥር 10 እና 11 ላይ ላሉት በድርጅቱ የውስጥ አሠራር መሠረት የሽያጭ ውል የሚደረግባቸው ከመስከረም 4 ቀን 2019 (Sep 14,2026) ጀምሮ ሲሆን ድርጅቱ ዕቃዎቹ በሚጠራቀሙበት ጊዜ ሲያሳውቅ ክምችቱን በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው። በተጨማሪም ከተ/ቁ 11-19 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች አሸናፊ እንደተገኘ የሽያጭ ውል ከተፈጸመ በኋላ ድርጅቱ ዕቃዎቹ በሚጠራቀሙበት ጊዜ እንዲያነሱ ሲያሳውቅ ክምችቱን በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው እንዲሁም ከተራ ቁጥር 11-19 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በሶስት (3) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን የማንሳት ግዴታ አለባቸዉ።

ቀ) ከተራ ቁጥር 2-7 ለተገለጹት የዕቃ ዓይነቶች ለሚጫረቱ ተጫራቾች በአዋጅ ቁጥር 1090/2010 መሰረት ለአደገኛ ቆሻሻዎች በዋናነት ጥቅም ላይ ለዋሉ የተለያዩ ዘይቶች፣ነዳጅ፣ናፍጣ እና ባትሪዎች በሚል ከኢፌዴሪ ጥበቃ ባለስልጣን የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንዲሁም ተራ ቁጥር 1፣12 ፣ እና 13 ላይ ለተጠቀሱት በደንብ ቁጥር 425/2010 መሰረት ከኢፌዴሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተሰጠ ሰርተፍኬት በተጨማሪም ተራ ቁጥር 8 ለተጠቀሰው በአዋጅ ቁጥር 299/2002 መሰረት በሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የፀደቀ የአካባቢ እና የማህበረሰብ ተፅዕኖ ግምገማ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ፥

ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 እና በተራ ቁጥር 12 እና 13 ለተዘረዘሩት እቃዎች ማንኛውም ተጫራች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖረው መወዳደር አይችልም በተጨማሪም ከቀበሌ፣ ከወረዳ ፣ከከተማ አስተዳደር እና ከክልል የአካባቢ ጥበቃ ቢሮዎች የተሰጡ የድጋፍ ደብዳቤዎች፣ የአካባቢ እና ማህበረሰብ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርቶች እንዲሁም ከአዋጅ 1090/2010 እና ከደንብ 425/2010 አግባብ ውጭ የሚቀርቡ ሰርተፍኬቶች ተቀባይነት አይኖራቸውም። 

በ) ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሊገዙ በሚመጡበት ጊዜ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች።

1. የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (2018 ዓ/ም) (ለተዘረዘሩት ሁሉም የዕቃ ዓይቶች)።

2. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 11 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሠርተፊኬት ሠነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ሠነዱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል።

3. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 እና በተራ ቁጥር 12 እና 13 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የአካባቢ ጥበቃ ሴርተፊኬት ሠነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ሠነዱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል።

4. ማንነታቸውን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፤ፓስፖርት ወይንም የታደሰ መንጃፈቃድ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡ (ለተዘረዘሩት ሁሉም የዕቃ ዓይነቶች):: የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን የጨረታ ሠነድ በሚገዙበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ለማያሟላ ማንኛውም ተጫራች ሠነድ የማንሸጥ መሆናችንን እንገልጻለን።

ተ) ተጫራቹ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት በሚሆንበት በጨረታው ለመሳተፍ የቀረበው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያስረዳ ሰነድ (በሚመለከተው አካል የተመዘገበና የጸደቀ የመመስረቻ ፅሁፍ እና/ወይም ቃለ ጉባኤ) እና የድርጅቱን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል።

ቸ) የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ዋጋ መሰረት በጨረታ ማስታወቂያው ወይም በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እቃውን ባይወስድ/ባያነሳ፤ ክፍያ ባይፈጽም፣ (ውል በሚያስፈልግበት ግዜ ውል ለመፈጸም ፈቃደኛ ባይሆን) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ወዲያውኑ ይሰረዛል፤ እንዲሁም ጨረታው በድጋሚ በሚወጣበት ወቅት የዋጋ ልዩነት ከመጣ ልዩነቱን እንዲከፍል ይገደዳል፤

ኀ) ማንኛውም አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚያነሳበት ጊዜ ዕቃዎቹን መምረጥ አይችልም።

ነ) በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘበ (Bid Bond) በሚቀጥሉት ሁለት (2) የሥራ ቀናት ተመላሽ ይሆናል።

ኘ) ከተራ ቁጥር 1 እስከ 9 እና ተራ ቁጥር 12 ፣13 ፣15፣16 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች አሸናፊወች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመስክ ምልከታ(Facility Visit)እንደሚደረግ እና መስፈርቱንእማያሟሉ ከሆነ የሽያጭ ውል የማይፈፀም መሆኑን እናሳውቃለን::እንዲሁም ከተ/ቁ 8 እና 19 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ቆራርጦ እና ፈጭቶ መጠቀሙን ማሳየት የሚችል መሆን አለበት።

አ)የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ዋጋ መሰረት አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ከአየርመንገዱ የወሰደውን ጥቅም ላይ የዋሉ እቃዎችን ለተፈለገው አላማ እያዋለ መሆኑን ለማረጋግጥ በቅድሚያ በማሳዎቅ ወይም ሳያሳውቅ/ድንገተኛ የመስክ ምልከታ እንደ አስፈላጊነቱ ያከናውናል።

ከ) ድርጅቱ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ እና ሰነድ ለመግዛት እነዚህን ስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተረከቡትን ማንኛውንም ያገለገሉ እቃዎች በተሻለ አካባቢያዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በሚሰጥ መልኩ የሚያስወግዱ፣ ጥቅም ላይ የሚያውሉ እና የላቀ አቅም ያላቸው ህጋዊ ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ። ይህም ተፈጻሚ የሚሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የሚመጣጠን አገልግሎት በውሉ መሰረት ለመስጠት አቅም ያላቸው መሆኑን የሚያስረዱ ሰነዶች ለምሳሌ የጭነት አገልግሎት መኪኖች ባለቤትነት፣በቂ የሰው ሃይል(በዉል የተደገፈ)፣የተደራጀ የአሰራር ዘዴ(ፖሊሲ፣ማኑዋል፣መመሪያ)፣ በቂ ማሽነሪ እና የስራ ቦታ ይዞታ ሰነዶች ወይም ማስረጃዎችን ማቅረብ ሲችሉ ብቻ ነው።

ሥልክ ቁጥሮች + 251-115-17-88-24 /+ 251-115-17-87-81


Tender details

  • Deadline: 2026-08-14
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-08-14 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 600.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
  • Posted at: 2026-07-25T08:25:21.000Z
← Back to all tenders