Audio-visual, photography and graphic design

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪከት የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳደሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪከት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ከወ/ሪት ፅዮን ጌታቸዉ የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሠረት የኪራይ ከፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳደሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የንብረቱ ዝርዝር

ብዛት በቁጥር

የጨረታው መነሻ ዋጋ

የንብረቱ ሁኔታ

የጨረታው ሁኔታ

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

Baking Rotary Oven with Burner

Brand: PORLANMAZ model: PMDF200, Origin-Turkey

1

10,370,520.08

አዲስ

ዝግ ጨረታ

ሐምሌ 20 ቀን 2018 .. ጠዋት ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

 

2

Mixer

Brand: PORLANMAZ, Model:  PMSP210,Origin Turkey

1

3

Dough Divider

Brand: PORLANMAZ

Origin: Turkey

1

4

Dough Moulder Machine

Brand: PORLANMAZ

Model: PMD350 Origin: Turkey

1

5

Proofer with Steam Generator

Brand: PORLANMAZ

Model: Origin Turkey

1

6

Trolley with 16 tray

Brand: PORLANMAZ

Number of pans per trolley - 16

material stainless steel

4

7

Bread Slicer

Brand: PORLANMAZ,

Model: PMDS500, Origin: Turkey

1

8

Sound Proof Generator

Brand: AKSA, Model:

AP33, Rated power: 33KVA

1

የዝግ ጨረታው መመሪያ

1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻን በመጥቀስ ፣የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር 2,074,104.11 /ሁለት ሚሊዮን ሰባ አራት ሺ አንድ መቶ አራት ከ አስራ አንድ ሳንቲም/ የያዘ በኢ/ት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒ (CPO ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገዢዉ የሚገዛበትን ዋጋ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢ/ት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ማመልከቻውን ማስገባት ይችላል።

2. ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ፤ መናኸሪያ ከ ከተማ፤ ጉዊ ቀበኪ ባንኩ ከሀዋሳ ጨርቃጨርቅ ሸማ በተከራየው መጋዘን ውስጥ ነው።

3. ማንኛውም ንብረቱ ለመግዛት ያሸነፈ ተጫራች 15% ተእታ ቫት ይከፍላል።

4. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች

4.1 የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል፣

4.2. ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማቅረብ ያስፈልጋል ወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈልገውን የጉምሩክ ቀረጠና ታክስ የመክፈል ግዴታ አለበት፣

5. የዝግ ጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካለከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡ ለተሸነፉ ተጫራቾች ከጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ወዲያወኑ ይመለስላቸዋል፡፡

6. ንብረቱን በባንኩ ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀከት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል፣

7. የዝግ ጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተግጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማተዳደር የሚወጡ ወጪዎችን ማለትም የመጠለያ ኪራይ ፣የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት፣

8. የዝግ ጨረታዉ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ካለበት መጋዘን ወደሚፈግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ ጉዞ ኢንሹራንስ ፤ መትከያ ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል።

9. የዝግ ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋት 4፡00 አስከ 6፡00 ሰባት በኢ/ት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ምርከአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደርጋል።

10. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ከማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደወሎ ማነጋገር ይቻላል፣

11. ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መነበኘት ይቻላል።

12. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-26 10:00
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20% ብር 2,074,104.11 /ሁለት ሚሊዮን ሰባ አራት ሺ አንድ መቶ አራት ከ አስራ አንድ ሳንቲም/
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T08:06:10.000Z
← Back to all tenders