Spare parts and accessories

ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ

ቁጥር:OIT/N/Bid-01/2019

ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር የተሽከርካሪ ጎማ(315/80R22.5)እና መለዋወጫዎች(ለተሽ/ ሞደል-VOUVO Bus-B11R Viago/1050/ 2019) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ገዝታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡-

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳድሩ ተጋብዛችኋል፡

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ::

2. የግብር መለያ ቁጥር(TIN) ያለውና የቫት(VAT)ተመዝጋቢ የሆነ።

3. ለጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO/un Conditional Bank Guarante) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ::

4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14(አሥራ አራት)ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ) ከፍለው ከኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አማ መከኒሣ በሚገኘው ኤስ-ሳራ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ከግዢ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።

 5. ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) በመሙላት ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈር ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ15ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው የሚከፈትበት 15ኛው ቀን እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

7. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን 4:30 ላይ መከኒሣ በሚገኘው በድርጅቱ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል በይፋ ይከፈታል::ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይሳተፉም የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም::

8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የመወዳደሪያ ሀሳብ መቀየር ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታው መውጣት አይቻልም::

9. አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታው ውጤት ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ከውል ሰጪው ጋራ ተስማምቶ መፈረም ይኖርባቸዋል::

10.ከአሸናፊ ተጫራች በሚደረገው ውል መሰረት፣የሚያቀርቡት የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ በተጠየቀው መሥፈርት በራሱ ትራንስፖርት ገላን በሚገኘው በድርጅቱ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ለንብረት ክፍል ገቢ የሚያደርግና የመለዋወጫዎች ብዛት ሊጨምርም ሊቀነስም ይችላል።

11.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት
አክስዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-10 12:00
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ODAA Integrated Transport Share Company
  • Buyer address: Addis Ababa, Sub city: Nifas Silk Lafto, woreda 02, Mekannisa S.Sara Tower 5th Floor, around Amigo Caffe,
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T08:17:32.000Z
← Back to all tenders