Vehicle and Machinery Foreclosure
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
|
የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) |
ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት |
||||
|
የሰሌዳ ቁጥር |
ሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የንብረቱ አይነት |
የሥሪት ዘመን |
|||||
|
1 |
አልፋ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው
|
AA-03-A83556 |
MA3AVC71S00395411 |
K15BN1069432
|
አዉቶሞቢል
|
2019 |
2,751,756.00
|
05/12/2018 ዓም 3፡00-4፡00 ጠዋት |
|
2 |
ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ወንድም ፈለቀ |
አአ-02-C33705 |
G4LANM14995
|
MALB241C8NM149028 |
ሃዩንዳይ ግራንድ 10 አውቶሞቢል |
2022 |
3,098,304.00
|
05/12/2018 ዓም 4፡00-5፡00 ጠዋት |
|
3 |
አቶ ናስር ካሊል ሞሐመድ |
ተበዳሪው |
02-AA-B76699 |
JFC92432 |
1FTEX1EP1JFC92432 |
ፎርድ F150 ኪንግ ካፕ |
2018
|
4,765,200.00
|
05/12/2018 ዓ.ም 5፡00-6፡00 ጠዋት |
|
4 |
ኳድራንት አፓርል ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው |
ኢት-03-66900 እና ኢት-03-20264 |
F3BEE681G *B220222647*
|
WjME3TRE8EC286633 እና TT-1044-14
|
የጭነት እና ተሳቢ ተሽከርካሪ
|
2014 |
11,033,376,00 |
05/12/2018 ዓ.ም 8፡00-9፡00 ጠዋት |
|
5 |
ወ/ሮ ዉዳሴ አበበ ቸኮል
|
ቴዎድሮስ አበበ ቸኮል |
AA-02-B52539 |
FEAJ11.HRA *696746A* |
SJNFEAJ11U L2399086 |
አዉቶሞብል |
2018 |
2,673,000.00 |
05/12/2018 ዓ.ም 9፡00-10፡00 ጠዋት |
በመሆኑም፡-
1.ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።
2. ጨረታዉ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነዉ።
3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
4. ለጨረታ የቀረበውን ንብረት በጨረታ አሽንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።
5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
6. ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።
7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
8. ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቱን ካልተረከበ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 113-0508 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሰዓት ይለያያል
- Bid opening: 2026-08-11 16:00
- Bid opening (note): የጨረታው ሰዓት ይለያያል
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T11:25:41.000Z
- Buyer website: https://www.combanketh.com