Disposal, scrap and surplus sales

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የቢሮ ማሽኖች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

አንበሳ ባንክ

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር/003/2018 ግልጽ ጨረታ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የቢሮ ማሽኖች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ-ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 - 11:00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 - 6:00 ሰዓት የማይመለስ ብር 230.00 (ሁለት መቶ ሰላሳ ብር) ከባንኩ ዋና መ/ቤት ስር በሚገኘው የካ ቅርንጫፍ በመክፈል ከሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ።

1. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት በሰንጠረዡ በተጠቀሰው መሰረት ይሆናል።

 

የእቃው አይነት

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች

ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00

 

ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15

2

የቢሮ ማሽኖች

3

የቢሮ ፈርኒቸሮች

4

ሎች

2. ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ በክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም አሰርተው በታሸገ ኢንቬሎፕ ከነሙሉ አድራሻው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውንም ተጫራች የሚገዛውን የንብረት አይነት በመጥቀስ በባንኩ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሞልቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

5. የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ ግልፅ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል:: ስርዝ ድልዝ የተደረገበት ዋጋ ከሆነ በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ፈራሚ አካል ፓራፍ/ኢንሺያል ፊርማ ማድረግ ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል እንዲሁም ከቫት በፊት እና በኃላ መሆኑ መግለፅ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ንብረቶቹን ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 - 10:00 እና ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30- 5:30 ቀደም ብሎ ቀጠሮ በማስያዝ ቃሊቲ በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ ሪከቨሪ ጊቢ ውስጥ፣ ከደራርቱ አደባባይ ወደ አያት ጣፎ በሚወስደው መንገድ ከለሚ ኩራ ፖሊስ ጣቢያ ከፍ ብሎ እና ቦሌ መድኃኒዓለም ማፊ ሞል አጠገብ በሚገኘው የባንካችን ህንፃ ቤዝመንት ወለል ማየት ይቻላል።

8. ጨረታው 22 አካባቢየቀድሞ ዘሪሁን ህንፃ ፊት ለፊት ሌክስ ፕላዛ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በአንበሳ ባንክ ዋና መ/ቤት 4ኛ ወለል ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይክፈታል።

9. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ በመፈፀም ያስያዙትን ሲፒኦ (CPO) መውሰድ የሚችል ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 3 (ሶስት) የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ይመለስላቸዋል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ሃንዘቡን ለባንኩ ክፍለው ንብረቱን በ3 ቀናት ውስጥ መረከብና ማንሳት ይኖርባቸዋል።

11. በተባለው ጊዜ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉም ሆነ ገቢ አድርገው ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒኦ/ ለባንክ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንደ አስፈላጊነቱ ለሁለተኛ አሸናፊ ወይም በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።

12. አሸናፊ ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላሉ።

13. ስለእያንዳንዱ ንብረት ዝርዝር እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አማ ዋናው መ/ቤት ግዥ እና ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስስክ ቁጥር 0116-36-20-64/ 0919768134/ 0913581240/ 0923780251 ይቻላል።

14. ባንኩ ስለንብረቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሽያጩን በሙሉም ሆነ በክፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አንበሳ ባንክ አ.ማ

ዋና መ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-10
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-10 14:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lion International Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 230.00 ብር
  • Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T13:10:39.000Z
← Back to all tenders