Passenger and staff transport
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አርባምንጭ ቅርንጫፍ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አርባምንጭ ቅርንጫፍ የመ/ቤቱ ሠራተኞችን ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት በደረጃ(አንድ) በደረጃ(2)ሁለት እና በደረጃ(3)ሶስት ከተደራጁ ህጋዊ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ማህበራትን በጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የጨረታውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000498682492 የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ገቢ በማድረግ የባንክ ሊልፕ በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ ሰነድ ከጠቅላላ አገልግሎትና ንብረት አስተዳደር ሥራ ክፍል ቀርባችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።
መስፈርቶች፡-
1. በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ንግድ ሥራ ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ፣ የግብር መክፊያ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት እና በማህበሩ ስም የታተመ ደረሰኝ ኮፒ ሠነድ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ካሉ ይበረተታሉ::
2. ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ደረጃ (1)፣(2) እና ደረጃ(3) ሆኖ ባለ 45 ወንበርና ከዚያ በላይ የሚችል ሆኖ ብዛት/1/ ሲሆን በጨረታ ውድድር ደረጃ ከደረጃ፣ ደረጃ2፣ ከደረጃ2 እንዲሁም ደረጃ3 ከደረጃ3 የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተሽከርካሪ መሆን አለበት፡፡
3. ማህበሩ ለወድድር ሲቀረብ የማህበሩን ደረጃና ብቃት የሚገልጽ ወቅታዊ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO 20,000.00/ ሃያ ሽህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው።
5. የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ በአርባምንጭ ከተማው ውስጥ ባሉ በተመረጡ ፌርማታዎች ተንቀሳቅሶ በቀን ጠዋት 2 ዙር እና ከሰዓት 2 ዙር በአጠቃላይ በቀን 4 ዙር ወይም በቀን ውስጥ 50 ኪ.ሜትር ያህል ተንቀሳቅሶ አገልግሎት ለመስጠት የሚችል።
6. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ፡- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 10 ሥራ ቀናት፡፡
7. ጨረታ የሚታሽግበት ቀን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 10 ሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፉ መ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።፡
8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ የማህበሩ ክብ ማህተም እና ፊርማ መኖር አለባቸው፡፡
9. የመወዳደርያ ሰነድ የሚቀርበው በሰም በታሸገ ፖስታ ሲሆን በተጫማሪ የማህበሩ ክብ ማህተም በፖስታው ላይ መኖር አለበት፡፡
ማሣሰቢያ ፦
1. አሸናፊው ማህበር ከተረጋገጠ በኋላ የሚቀረበው ተሽከርካሪ ደረጃ ብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም የመድህን ዋስትና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከውል በፊት ማቅረብ አለበት።
2. ነዳጅና ተጓዳኝ ወጪዎች ሙሉ በሙሉ በአቅራቢው/በተጫራች ማህበር የሚሸፈን መሆኑን እናሳውቃለን።
3. የነዳጅ ዋጋ እንደ ሀገር በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምር ከሆነ እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ ከመ/ቤቱ ጋር በሚደረስ ስምምነት መሠረት ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
4. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ጎን፡፡
ስልክ:-046 181 1273/046 181 0380/046 181 0614/046 181 0539
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አርባምንጭ ቅርንጫፍ
Tender details
- Deadline: 2026-08-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 10 ሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-08-08 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 10 ሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service
- Bid bond: 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T08:20:22.000Z