Oromia
የወርቃ አካባቢ ሁለገብ የማ/ኅ/ሥ/ማህበር ሃላፊነቱ የተወሰነ የጭነት መኪና አፍ አሴ አር /FSR/ በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የወርቃ አካባቢ ሁለገብ የማ/ኅ/ሥ/ማህበር ሃላፊነቱ የተወሰነ የጭነት መኪና አፍ አሴ አር /FSR/ በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳሰብን
የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
1. ማንኛዉም ተጫራች ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አፍ አሴ አር/ በሚገኝበት አድራሻ በአካል በመገኘት መመልከት የሚችል ይሆናል።
2. ተጫራቾች በሚገዙት አፍ አሴ አር/ ከጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ (5%) የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለ 30 ቀናት የሚቆይ ዋስትና አሰርተው ማስገባት ይኖርባችዋል።
3. የተሰራበት ዘመን /ሞዴል/ 2009
4. የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 5,000,000.00 (አምስት ሚሊየን ብር ) ነው።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ መግዣ የሚውል 500 የማይመለስ ብር (አምስት መቶ ብር) ለመህበረ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባችዋል።
6. የጨረታ ማስከበርያ ዋስትናው ለ አሸናፊዎች ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።
7. ማንኛውም ተጫራቾች የተሳሳተ መረጃ ማቅረባቸዉ ከተረጋገጠ ማህበሩ ከዉድድሩ ማሰናበት ይችላል።
8. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ጫረታውን ካሸነፉበት ቀን አንስተው በ አምስት(5) ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን ከጨረሱ ቡሃላ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
9. የሰነድ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን ከ20/11/2018 እስከ 11/12/2018 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ10/12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዛው እለት በ 4፡30 የማህበሩ ቦርድ አባላት እና ተጫራቾች ተወካዮቻቸው /በተገኙበት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች በሚገዙት ሰነድ ውስጥ ስም እና ሙሉ አድራሻ በግል በማስቀመጥ ፍርሚያውንና ማህተሞን መምታት አለባቸው።
11. ተጫራቾች ለሽያጭ በሚቀርበው ሰነድ ሙስጥ ተጨማሪ ማብራርያ ማግኘት ይችላሉ።
12. ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው አድርገው መስራት አለባቸው / ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹ ተወካዩ ፊርማ ከፊለፊቱ መኖር አለበት። እንዲሁም ደግሞ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትናውን እና ሰነዱን በአንድ ፖስታ አሽገው በማህተም በማረጋገጥ አሽገው ማስገባት አለባቸው።
13. ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ጫረታውን ያሸነፈ ተጫራች የ ንብረት ስም ዝውውር በሚያደግበት ሰእት ቨትNAT/ ጨምሮ ወጪውን በራሱ የሚሸፍን ይሆናል።
15. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አፍ አሴ አር መኪና/ንብረቱን/ ሲረከብ ከነ ሙሉ እቃው ይሆናል።
16 የምዝገባ ቦታ ም/ዕ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ራያ ዋከና ህ/ሥ/ዩንየን ወይም ዎ ም/ዕ አርሲ ዞን 'ነንሰቦ ወረዳ ወረቃ ከተማ ወርቃ አካባቢ ሁለገብ የዝ/ኅ/ሥ/ማህበር ጽ/ት የምዝገባ ሰዓት ጠዋት 2፡30-6:30 ከ ሰዓት ከ 7:30–11፡00 የስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
አድራሻ ኦሮሚያ ክልል 'ም/ዕ አርሲ ዞን 'ነንሰቦ ወረዳ ወረቃ ከተማ 01 ቀበሌ ፓሊስ ጣብያ ፊት ለፊት ይገኛል ።
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር 0923869930/ 0916383582/ 0912930258/ 09048046230/
የወርቃ አካባቢ ሁለገብ የገ/ኅ/ሥ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-16
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-16 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: የወርቃ አካባቢ ሁለገብ የገ/ኅ/ሥ/ማኅበር
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T09:18:57.000Z