Amhara
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የICT እና ኢንተርኔት እቃዎችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ መለያ ቁጥር አብክመ
/ኢቴቢ/ግ/ጨ/01/2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ
- (ሎት 1 የICT እና ኢንተርኔት እቃዎችን) በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የሎት 1 ተወዳዳሪዎች ከተ.ቁ 1- 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ሰነዳቸው ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በሌላ ፖስታ በማሸግ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ብለው ለያይተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ግዥ የሚፈፀምላቸውን እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specifications/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid bond/ የሚወዳደሩበትን ሎት (ግዥ) ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ | C.PO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በቢሮው ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ተዘግቶ በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል።
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል (በሎት) ዋጋ ይሆናል።
- በአንድ ሎት ላይ በከፊል ዋጋ ሞልቶ መወዳደር ከዋጋ ውድድር ውጪ ያደርጋል።
- ተጫራቾች በዋጋ መሙያም ሆነ በቴክኒካል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አለማድረግ ከውድድር ውጪ ያደርጋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0583206856በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
ባህር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-11 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T09:39:31.000Z