Amhara
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በአዘዞ ክ/ከተማ ለደረስጌ ጤና ኬላ ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በአዘዞ ክ/ከተማ ለደረስጌ ጤና ኬላ ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾችመወዳደር የሚችሉመሆኑን እየገለፅን፦ ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡-
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
- የግብርመለያ ቁጥር ያላቸው
- ከደረጃ 6 እና በላይ የሆነ
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚሰራውን ስራ ዝርዝር መግለጫ(BOQ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን/ከ/አስ/ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት በጎንደር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጥሪአችንን አክብረው ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- ለግንባታ ስራዎች የፋይናንስ ግምገማ የተወዳደሩ ተጫራቾች ቁጥር ቢያንስ 3 እና በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ከ3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1% ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ መ/ቤታችን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
- ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን ከተ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡ 058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ
መምሪያ በጎንደር ከተማ አስተዳደር
ጤና መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-18 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T10:05:02.000Z