External audit and assurance
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ በማሰራት ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓትና ቦታ በግልፅ ይከፈታል፡፡ ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን /+251925750633/0913497204 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-08-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-06 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T10:41:43.000Z