Spare parts and accessories
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመኪና መለዋወጫ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካይነት ለሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየአንዳንዱ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ረዳት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ከሐምሌ 20/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን በተከታታይ ቀናት እስከ ነሐሴ 05/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ነሐሴ 5/2018 ዓ/ም በ16ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን 4፡00 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- ማንኛዉም ተጫራች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ዕቃውን በፍጥነት ማቅረብ ይኖርበታል።
- የመኪና መለዋወጫ እቃ የሚለየዉ በሎት ድምር መሆኑን መታወቅ አለበት።
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ በሥራ ሰዓት ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 0632 መደወል ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡ ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም
የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-08-11 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: East Dembia Woreda FEDB
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T06:18:34.000Z