Amhara
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ አስተዳደር የቢሮ ግንባታ 3ኛ ፊዝ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ማስገንባት ይፈልጋል
Description
በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ አስተዳደር የቢሮ ግንባታ 3ኛ ፊዝ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለዚህ፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፣ የብቃት ማረጋገጫና ተጨማሪ እስት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ። እንዲሁም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚፈልጉ ከሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። በተጨማሪም የግንባታውን ሥራ ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ከሐምሌ 20/2018 እስከ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ።
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በ22ኛዉ ቀን ነሐሴ 11/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት እና 3፡31 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለዉ።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- ማንኛዉም ተጫራች (ተወዳዳሪ) አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በፍጥነት ወደ ግንባታ ሥራው መግባት አለበት።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከደረጃ 6 (ስድስት) እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸዉ።
- የሞላዉ ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከመሐንዲስ ግምቱ 25 በመቶ በታች ሞልተዉ የሚያቀርቡ ተጫራቾች አሸናፊ ሆነዉ ወደ ስራ ሲገቡ ዝርዝር የግንባታ ዋጋ (cost Break down) እና የግንባታ መርሃ ግብር (project Work Schedule) እንዲሁም ባቀረበዉ የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ (Conformation Letter) አሸናፊነቱ በተገለጸ በ5 የሥራ ቀናት ዉስጥ የማቅረብ ግዴታ ያለበት። ይህን ማድረግ ካልቻለ ከዉድድር ዉጭ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊ ተጫራች ዉል ይዘዉ ወደ ሥራ ሲገቡ ቅድመ ክፍያ የማይከፈላቸዉ መሆኑን እና የሚያሲዙትም 25 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ሲፒኦና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ መሆን አለበት።
- በየአንዳንዱ ቢልኦፍ ኳንቲቲ የተጋነነ ከፍተኛ ዋጋ የሞሉ ተጫራቾች ከማሃንዲሱ ግምት በላይ የሞሉት ዋጋ ሥራዉን ቢሰሩም ሳይከፈላቸዉ እንደሚቆይና ጨርሰዉ ሲያስረክቡ የሚከፈላቸዉ ይሆናል።
- የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) በግዥ ፈፃሚዉ መ/ቤት ባለሙያ ከሚያስተካክለዉ ዉጭ በተጫራቾች የሚቀርበዉ የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ዉጭ ይሆናል።
- በመመሪያ ክፍል ሁለት አንቀጽ አራት ፊደል ረ ተራ ቁጥር 2 ላይ ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች በቁጥር ቢያንስ ሶስትና ከዚያ በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበዉ አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረዉ ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከዉድድር ዉጭ የሚሆኑ ሲሆን እንዲሁም ከ3 በታች ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበዉ አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረዉ ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል።
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 0632 መደወል ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ ተጫራቾችን አይመለከትም።
የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 09:31
- Bid opening: 2026-08-17 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: East Dembia Woreda FEDB
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T06:23:02.000Z