Amhara
ሱታና የንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የተለያየ መጠን ያለው ብሎኬት፣ አሸዋ ፕሌቶች (ብረትና ጆ ቮልት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 01/2019 ዓ/ም
ሱታና የንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያለው
- ብሎኬት፣
- አሸዋ ፕሌቶች (ብረትና ጆ ቮልት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።
- በጨረታዉ መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ሱታና ንግድና ማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ ስራ ክፍል በመውሰድ እና ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 001 የምትጫረቱትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ። የሚገዛዉ ዕቃ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ሆነው ለሚገዛው እቃ በኪው አር ኮድ በታተመ ደረስኝ የሚሰጥ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለአሸዋና ብሉኬት 50‚000.00(ሃምሳ ሽህ ብር) ቦልት ጆ ቮልትና ፕሌት ብር 20‚000 (ሀያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ ወይም በሁኔታ ሳይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፋቸዉን ውሎች መያዝ አለባቸዉ።
- የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ፤ጨረታዉ በ11 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ቀን አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም ለጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ። ሰነዱን የወሰዱት ሁሉም ተጫራቾች ከመከፈቻ ቀን በፊት ሁሉም ከመለሱልን የመክፈቻ ቀን ሳንጠብቅ የሚከፈት ይሆናል።
- አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ7 ቀን በኋላ ባሉት 8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት።
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡።
- አሸናፊዉ ድርጅት በግዥ መመሪያው መሰረት የቅድመ ግብር ሶስት በመቶ እንደሚቆረጥበት ታሳቢ ተደርጎ ዋጋውን መሙላት አለበት።
- ኢንተርፕራይዙ ባወጣው ጨረታ ላይ 50 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 42 26 44 ይደዉሉ።
- አድራሻ በአዊ አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ፣ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርኘራይዝ ነዉ።
ሱታና የንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-08-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛዉ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-06 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛዉ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Sutana Trading and Consultancy Enterprise
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T06:30:32.000Z