Spare parts and accessories

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር: ጣበስፋ / አግ/ ብግጨ / 01/2018/19

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ

  • በሎት 1 የተለያዩ ትራክተሮች መለዋወጫ ዕቃዎች
  • በሎት-2 የተለያዩ ዶዘሮች እና ዊልዶዘሮች መለዋወጫ ዕቃዎች እና
  • በሎት-3 የተለያዩ ገልባጭ መኪናዎች፣ ሃይቤድ እና ሎውቤድ መለዋወጫ ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. ጨረታው ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000057735167 በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ.4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

4. የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።

አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ
ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 558 6725
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።

7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው።

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-558-6725 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-11 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tana Beles Sugar Factory
  • Buyer address: ካሳንቺስ ከመናኸሪያ ሆቴል  ወደ አቧሬ አቅጣጫ በሚወስደው አስፓስት መንገድ ከጨርጨር ስጋ ቤት ዝቅ በማለት የቀድሞው ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ጊቢ ውስጥ
  • Bid bond: 2% በየሎቱ
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T08:18:07.000Z
← Back to all tenders