Disposal, scrap and surplus sales

ዓባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር አሕየወፓ-ሽ 05/2018

ዓባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ የተለያዮ ህትመቶች በሚሰራበት ወቅት የተረፈ ምርት ውጤቶች ማለትም 80 ግራም ህትመት የተሞከረበት ወረቀት ፕሌት ከነ ቁርጥራጮ፣ 80 ግራም ወረቀት፣ 60ና45 ግራም ግልፋፊ ወረቀት፣ ኮር የወረቀት መጠቅለያና የላምኔሽን መጠቅለያ ጨምሮ በተለያየ መጠን የተቆራረጠ ላምኔሽን 60፣ 60ና 45 ግሪም ቁርጥራጭ ወረቀት የመጽሃፍ ከቨር፣ መጽሃፍ፤ ፓስ ቡኮች፣ የፕላስቲክ ገመድ (ዘንቢል መስሪያ የሚሆን) የ ካርቶንና የአርት ወረቀት ተጠቅልሎ የሚመጣበት ካኪወረቀት፣ የኮር ቀለበት፤ የመጽሃፍ መስፊያ ሽቦ ተጠቅልሎ የሚመጣበት የሽቦ መጠቅለያ ወረቀት ተጠቅልሎ የሚመጣበት የተለያየ አይነትና መጠን ያላቸዉ ፕላስቲክ ፊስታል፤ ባለ 5 ሊትር ጀሪካን ባለ 3 ሊትር ጀሪካን፣ ክዳን የሌለዉ ባለ 3 ሊትር ጀሪካን፤ ክዳን የሌለዉ ባለ 5 ሊትር ጀሪካን፣ የተለያየ መጠን ያለዉ ያገለገለ ብላንኬት፣ የተለያየ መጠን ያለዉ ያላገለገለ ንፁህ ብላንኬት፤ ብላንኬት ታሽጎ የመጣበት የካርቶን ቱቦ፣ የአልኮል የጎማ በርሚል 250 ሊትር የሚይዝ፣ ባለ 15 ሊትር የቀለም ጣሳ፣ ባለ 2ሊትር የቀለም ጣሳ፣ ፕሌት ክሊነር የመጣበት ባለ 1 ሊትር ጎማ ፣ የኮላ ቀረጢት ባለ 25 ኪሎ የሚይዝ እና አልኮል የመጣበት የብረት በርሚል ባለ 200 ሊትር የሚይዝ ባሉበት ሁኔታ እስከ ሰኔ 30/2019ዓ/ም የሚቆይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል

1. መወዳደር የሚችል ማንኛውም ድርጅት፣ ተቋም ወይም ግለሰብ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና (TIN) ያላቸው መሆን አለባቸው

2. ተረፈ ምርት የሚገኝበት ቦታ ማየት የፈለጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታዉ መዝጊያ ቀን ድረስ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።

3ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ የተጫራቾች መመሪያ የዉል ረቂቅ የዋጋ መሙያ ፎርምና ቴክኒክ መግለጫ ያያዘዉን የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ኢንዱስትሪ መንደር ከጣና ሞባይል አከባቢ ከሚገኘዉ ከፋብሪካዉ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ 4 ኪሎ አማራ ልማት ማህበር አዲሱ ሀንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 224 ከሚገኘዉ ከፋብሪካዉ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000281546078 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊ ከሆኑ ደግሞ የዉል ማስከበሪያ፣ 80 ግራም ህትመት የተሞከረበት ወረቀት፣ 60 80ና 45 ግራም ቁርጥራጭ ወረቀት፣ 80 ግራም ግልፋፊ ወረቀት፣ 60ና45 ግራም ግልፋፊ ወረቀ፣ ከዚህ በላይ ላሉት ለእያንዳንዱ የውል ማስከበሪያ 50,000ብር (ሃምሳ ሽህ ብር) ማስያዝ አለበት፣ እንዲሁም ከዚህ በታች ለተዘርዘሩት ለእያንዳንዱ ለኮር የወረቀት መጠቅለያና የላምኔሽን መጠቅለያ ጨምሮ፣ በተለያየ መጠን የተቆራረጠ ላምኔሽን፣ ፕሌት ከነ ቁርጥራጩ፣ የመጽሃፍ ከቨር ፣ መጽሃፍ፣ ፓስ ቡኮች፣ የፕላስቲክ ገመድ፣ ካርቶንና የአርት ወረቀት ተጠቅልሎ የሚመጣበት ካኪ/ወረቀት፣የኮር ቀለበት፣ የመጽሃፍ መስፊያ ሽቦ ተጠቅልሎ የሚመጣበት የሽቦ መጠቅለያ፣ ወረቀት ተጠቅልሎ የሚመጣበት የተለያየ አይነትና መጠን ያላቸዉ ፕላስቲክ /ፊስታል፣ ባለ 5 ሊትር ጀሪካን ፣ ባለ 3 ሊትር ጀሪካን፣ ክዳን የሌለዉ ባለ 3 ሊትር ጀሪካን፣ ክዳን የሌለዉ ባለ 5 ሊትር ጀሪካን፣ የተለያየ መጠን ያለዉ ያገለገለ ብላንኬት፣ የተለያየ መጠን ያለዉ ያላገለገለ/ንፁህ/ ብላንኬት፣ ብላንኬት ታሽጎ የመጣበት የካርቶን ቱቦ፣ የአልኮል የጎማ በርሚል 250 ሊትር የሚይዝ፣ ባለ 15 ሊትር የቀለም ጣሳ፣ ባለ 2ሊትር የቀለም ጣሳ፣ የፕሌት ክሊነር የመጣበት ባለ 1 ሊትር ጎማ ፣የኮላ ቀረጢት ባለ 25ኪሎ እና አልኮል የመጣበት የብረት በርሚል ባለ 200 ሊትር የሚይዝ 10,000ብር (አስር ሽህ ብር) ማስያዝ አለበት

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 60 (ስልሳ) ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት እንዲሁም የጨረታ ዋጋ በውሉ የፀና መሆን አለበት።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፋብሪካ ግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ሀምሌ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሀሴ 6 / 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ቢሮ ነሀሴ 6 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8.30 ሰዓት ይከፈታል። በመሆኑም ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል።

8, ፋብሪካዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው!

9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ሲያስፈልግ ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 321 8865 በመደወል ማግኘት ይቻላል፤

ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-12 14:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Abay Printing & Paper Packaging P.L.C.
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T14:49:13.000Z
← Back to all tenders