Disposal, scrap and surplus sales

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩከ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 29/11/2018 እና 02/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩከ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 29/11/2018 እና 02/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልከ ቁጥር 022 224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች፡-

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሲ እንቅሰቃሴያቸውን ለታከስማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 29/11/2018 እና 02/12/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።

3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ አንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሸ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4 ተጨራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የጨረታ ቦታ

የጨረታው ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታው መዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ

ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነዕር፣ ጌጣ ጌጦች፣ ጠፍጣፋ ብረት፣ ላሜራ የወዳደቁ ብረቶችና ፕላስቲኮች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች።

ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 29/11/2018 እና 02/12/2018 እስከ ጠዋቱ 3:45

 

ለግልጽ ጨረታ 29/11/2018   2/12/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00፣ የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ 29/11/2018 እና 02/12/2018 5፡00 ሰዓት ይሆናል።

5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

 6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፈ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ውሰጥ ተመላሸ ይደረግላቸዋል።

7. ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖረበታል።

8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውሰጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማሰከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሸያጭ ይቀርባል።

9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-08
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ቀን እና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-08-08 11:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ቀን እና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Revenue & Customs Authority Awash Branch
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
  • Posted at: 2026-07-30T08:54:09.000Z
← Back to all tenders