Oromia

የመኪና እና የእርሻ ትራክተር ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

የፍርድ ባለሙበት ዩሱፍ አብዶ የፍርድ ባለዕዳ አቶ ካልሐሪ ፋርም ኢንዱስትሪ PLC መካከል ያለውን የአፈጻጸም ከርክር አስመልክቶ 1ኛ ፒካፕ ሚትስቡሸ መኪና የሰሌዳ ቁጥሩ A3_32693 AA የሆነ፣ የሞተር ቁጥር 4D56U-CFB0167P32513 የሆነ የሻንሲ ቁጥር MMBJNKB40FD015480 የሆነ እና በአፈጻጸም ተከሣሽ ካልሐሪ ፋርም ኢንዱስትሪ ዞር ስም ተመዝግቦ ያለውን በጨረታ ማስታወቂያ መነሻ ዋጋው ስምንት መቶ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር ከዘጠና አምስት ሣንቲም (807,385.95) እና 2ኛ/ የእርሻ ትራክተር ብዛት ሁለት/2/ 2ኛ/ የሞተር ቁጥር LM9B602V514456A የሆነ የሻንሲ ቁጥር K72167 የሆነ እንዲሁም የእርሻ ትራክተር የሞተር ቁጥር LM9B602V514485A የሻንሲ ቁጥር K72168 እና በአፈጻጸም ተከሣሽ ካልሐሪ ፋርም ኢንዱስትሪ PLC ስም ተመዝግቦ ያለውን በጨረታ ማስታወቂያ መነሻ ዋጋው እያንዳንዱ ትራክተር መኪና ዋጋ አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሶስት ብር ከሃምሣ ሶስት ሣንቲም (469,693.53) የሆነ በአጠቃላይ ከዚህ በላይ የተገለጹት ሶስቱ/3/ መኪናዎች ፍ/ቤቱ ግልጽ በሆነ ጨረታ አካሂዶ መሸጥ ስለፈለገ፣ በዚህ ጨረታ ላይ ተሳትፈው የመግዛት ፍላጐት ያላቸው ሰዎች ከቀረበው ግምት ብር ላይ 1/4ኛውን አስቀድመው በባንክ CPO በማስያዝ በአዳማ ከተማ ደምበላ ክፍለ ከተማ ወንጂ ወረዳ በወንጂ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ መኪናዎቹ በቆሙበት በሚገኙበት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፣ የጨረታው ማስተወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ እስከ ቀን 22/12/2018 እስከ 12፡00 ሰዓት በአየር ላይ ቆይቶ በቀን 22/12/2018 ከምሽቱ 12፡00 ላይ ተዘግቶ በቀን 23/12/2018 3፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ተወዳዳሪዎች ፣ የጨረታ አጫራቾች እና ታዛቢዎች ባሉበት ተከፍቶ በቀረበው መነሻ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበው የሚሸጥ ወይም የሚካሄድ መሆኑን በማወቅ በአካል ቀርበው ተወዳድረው መግዛት እንደሚቻል የደምበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት አዟል።

ማሳሰቢያ

1. በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር ወይም ለመሳተፍ የመጣ የግምቱ መነሻ ዋጋ ላይ 1/4ኛ CPO ያስያዘበትን ለጨረታ ኮሚቴ ማቅረብ አለበት።

2. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ገንዘብ ዋጋ ጨረታው ከተካሄደበት ቀን አንስቶ በ5 ቀናቶች ውስጥ መክፈል መቻል ይኖርበታል።

3. ጨረታው የሚካሄደውበት ቦታ በወንጂ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ ነው።

4. የጨረታውን ውጤት በቀን 25/12/2018 4፡00 ሰዓት ላይ ይቀርባል።

5. የስልክ ቁጥር 0911840256 ላይ መደወል ይቻላል።

የደንበላ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የፍታብሔር ችሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 18:00
  • Bid opening: 2026-08-29 09:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደንበላ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
  • Posted at: 2026-07-30T09:29:46.000Z
← Back to all tenders