Disposal, scrap and surplus sales
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምሰሶ ተረፈ ምርት ቁርጥራጭ እንጨቶች ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-03/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ሎት
|
የሚወገደው ንብረት ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
የምሰሶ ተረፈ ምርት ቁርጥራጭ እንጨቶች |
ጎተራ
|
በሜኩ
|
465 |
30,000
|
ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 |
ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 |
|
2 |
የምሰሶ ተረፈ ምርት ቁርጥራጭ እንጨቶች |
ነቀምት
|
|
150 |
6,000 |
ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 |
ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር በፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን፤ መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።
2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሸን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኦከሽን ኢትዮጵያ አክሲያን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል።
4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና(Bid Security) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታዉን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር(Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
8. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፋችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል።
9. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊደረግ ይችላል።
10. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. የኦክሸን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 09-05-11-55-11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
12. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-1-11-98-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-08-18 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
- Posted at: 2026-07-31T07:53:29.000Z