Disposal, scrap and surplus sales

ጥላ ኤች.አይቪ በደማቸው ያለ ሴቶች ማህበር ከዚህ በፊት ይገለገልባቸው የነበሩ የልብስ ስፌት ማሽን፣ የሹራብ ማሽንና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና ያገለገሉ ላፕቶፖች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጥላ ኤችአይቪ በደማቸው ያለ ሴቶች ማህበር ከዚህ በፊት ይገለገልባቸው የነበሩ የልብስ ስፌት ማሽን የሹራብ ማሽንና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና ያገለገሉ ላፕቶፖች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟላት ይጠብቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሲያቀርብ በተለያየ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደሰ የሥራ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) ማቅረብ የሚችሉ

2. ተጫራቾች የጨረታ ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ እየከፈላቹ የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው መግዛት የሚችሉ 200 (ሁለት መቶ ብር) መሆኑን እንገልፃለን።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 20% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማስያዝ አለባቸው:

4. የጨረታ አካሄድ በመንግስት የግዥ መመሪያ መሰረት ይሆናል።

5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሀሳብ ተፈርሞበት በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያ ከተመለከተው የግዥ ገደብ በፊት ቀርቦ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

6. ጨረታው በማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ሀዋሳ ከተማ ወልደ አማኑኤል ዱባለ ጎዳና አላቲዮን የመ/ደ/ሆስፒታል ዝቅ ብሎ
ማሳሰቢያ ፡- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 212 2858/ 0916 511 023/0911 033 914
ጥላ ኤች.አይቪ በደማቸው ያለ  ሴቶች ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-11 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Tila H.I.V Positive Women Association
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
  • Posted at: 2026-07-31T08:01:05.000Z
← Back to all tenders