Books, manuals and publications
የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1-8ኛ ክፍል የተማሪዎች መጽሀፍት የህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1-8ኛ ክፍል የተማሪዎች መጽሀፍት የህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጨማሪ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሠረት ይሆናል።
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን እያንዳንዱን በብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰደ ትችላላችሁ።
2. ጨረታው በ16ተኛ ቀን የጨረታው ሳጥን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ሆኖም ግን በመክፈቻው ቀን የተጫራቾች ያለመገኘት መምሪያው ጨረታውን ከመክፈት የሚያስተጓጉለው ነገር አይኖርም።
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ ዋስትና በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
4. የጨረታው አሸናፊ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ 10% የውል ማስከበሪያ (CPO) ወይንም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርበታል።
5. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
6. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ተኛ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-19 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ተኛ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Halaba Zone Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
- Posted at: 2026-08-01T07:27:26.000Z