Disposal, scrap and surplus sales
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወልድያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ቤት ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሴሪያል ቁጥር ያላቸው ያገለገሉ ጎማወችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወልድያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ቤት ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሴሪያል ቁጥር ያላቸው ያገለገሉ ጎማወችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ከላይ በተዘረዘሩት የጨረታ ሂደቶች ላይ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆነዎ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቸው እንዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡
2. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ከ25/11/2018 እስከ 10/12/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ 300 ሶስት መቶ ብር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ወልድያ በሚገኘው በጥገና ጽ/ቤቱ ግዥ/ፋ/ን/አ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያውን የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ/ ለመ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
4. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆነዎ የሚያረጋግጥ የዋናውን ፎቶ ኮፒ በማያያዝ በፖስታ አሽገው እስከጨረታ መዝጊያ ቀንና ስዓት ድረስ በጥገና ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ካወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታና በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የድርጅትዎን ማህተምና አድራሻ ፊርማ በማድረግ ለመስሪያ ቤቱ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው 11/12/2018 ዓ.ም 4:00 ስዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ የተሟላ ከሆነ ይከፈታል::
7. ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎች ላይ ሁሉንም በጠቅላላ ዋጋ (በሎት) የሚሞላ መሆኑ የታወቅ፡፡
8. አሸናፊ ተጫራቾች ከታወቀ በኋላ ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች በጨረታው ግምገማ ውጤት ቅሬታ ካላቸው ውጤቱ በተገለጸበት በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
10. ጥገና ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ያወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ ከሰአት እሁድ ወይም የባአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
12. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በ 0993 360 439 ይደውሉ፡፡
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወልድያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-17 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Rural Roads Construction Agency
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
- Posted at: 2026-08-01T07:29:10.000Z