Oromia

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በዴሌ ዞን የዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በዴሌ ዞን የዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የግዥው ዓይነት

  1. የደንብ ልብሶች
  2. የጽህፈት (ስቴሽነሪ) መሳሪያዎች
  3. የጽዳት እቃዎች
  4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  5. ቋሚ የቢሮ እቃዎች (Furniture)
  6. የተለያዩ የመኪና ጎማዎችና የጎማ ካላማዳሪ
  7. የተለያዩ ሞተር ሳይክልና፤ የተለያዩ የሞተር ሳይክል ጎማዎች
  8. የቴክንክና ሙያ የህንፃ መሳሪያዎች
  9. የህትመት ሥራዎችን ለማቅረብ የሚከተለውን መስፈርት ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

መስፈርቱም፡-

1. በ2018 ዓ/ም በዘርፉ የወጣ ወይም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የ2018 ዓ/ም ግብር ስለመከፈሉ መስረጃ (ክሊራንስ) ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል።

3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

4. ተጫራች ቫት (VAT) ወይም ቲኦቲ (TOT) ተመዝጋቢ የሆነና TIN number ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ 20,000.00 (ሀያ ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

6. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባወጣው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ መሰረት ዋጋቸውን በትክክል ሞልተው በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማቸውን በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም አድርገው ሙሉ አድራሻቸውን በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ አለባቸው።

7. ግዥው ከ 20,000 ብር በላይ ከሆነ 3% የመንግስት ታክስ ያስከፍላል።

8. የሽያጭ ደረሰኝ ለእያንዳንዱ ሴክተር መ/ቤት መፃፍ አለበት።

9. ቫት ወይም ቲኦቲ (TOT) ጨምሮ ያልሰራ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካምሥራ አፈጻጸም የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር ፐርሰንት) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ አስራ አምስት (15) የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከዴጋ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።

12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒክ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንስ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቀን 27/11/2018 እስከ 15/12/2018 11፡20 ሰዓት ብቻ ዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት አለባቸው።

13. የጨረታ ሳጥን በቀን 15/12/2018 በ11፡30 ሰዓት ይዘጋል።

14. አሸናፊው ተጫራች የእቃውን ናሙና በውል መፈፀሚያ ጊዜ ማቅረብ ይኖርበታል።

15. የእቃው ማስረከቢያ ቦታ ዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታዎች ናቸው።

16. የጨረታ ሰነድ የሚከፈተው በቀን 18/12/2018 በ3፡30 ሰዓት በዴጋ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።

17. የእቃው ብዛት በ20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።

18. አሸናፊ ተጫራቾች የተጠየቁትን እቃ ሳያጓድሉ በአንድ ጊዜ ሲያስገቡ ብቻ ክፍያ የሚፈፀም መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

19. መሥሪያቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0913267331 ወይም 0966453135 መደወል ይችላሉ።

በቡኖ በዴሌ ዞን የዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid opening: 2026-08-24 09:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Dega Woreda FEDB
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T07:57:13.000Z
← Back to all tenders