External audit and assurance
የግንብ ገበያ ንግድ አክሲዮን ማህበር የ2018 በጀት ዓመት የፋይናንሻል የሥራ ክንውን በቻርተር የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂና የተፈቀደለት አዲተር (በውጪ ኦዲተር) ለማስመርመር ይፈልጋል
Description
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
የናዝሬት/አዳማ / የሚገኘው የግንብ ገበያ ንግድ አክሲዮን ማህበር የ2018 በጀት ዓመት የፋይናንሻል የሥራ ክንውን በቻርተር የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂና የተፈቀደለት አዲተር (በውጪ ኦዲተር) ለማስመርመር ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኦዲተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 5/12/2018 ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ሰነዳችሁን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግና የድርጅቱን ማህተም በመምታት በአካል በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ጨረታው ነሐሴ 5/12/2018 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ነሐሴ 5/12 /2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
1. የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ
2. የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ
3. TIN (የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
4. Vat/TOT ሰርተፊኬት
5. ስራውን ሰርቶ ለማቅረብ የሚፈጅበት የጊዜ ገደብ እና
6. የገንዘብ መጠን በግልፅ መታየት(መቀመጥ) አለበት
አድራሻ፡-አዳማ ከተማ መብራት ሀይል ገዳ ከ/ከተማ በዳቱ ወረዳ (በተለምዶ ሳር ተራ)በሚገኘው የማህበሩ ፅ/ቤት
B-Block 1ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን
ስልክ ቁጥር፡-022 211 3553
ሞባይል ፡-09 75 04 13 13/ 09 78 73 00 08
የግንብ ገበያ ንግድ አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-11 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ginb Gebeya Trading S.C
- Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
- Posted at: 2026-08-01T08:00:08.000Z