Building and equipment maintenance

በጉለሌ ክ/ከ/የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ በተለያዩ ሎቶች ማወዳደር ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር መ/አጠ/2ኛ/ት/ቤት /01/18

በጉለሌ ክ/ከ/የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ የሚከተሉትን ሎቶች ማወዳደር ይፈልጋል።

  1. የት/ቤቱ ክበብ እና የተማሪ ክበብ ለማከራየት 6233 ብር 35,123.20 /ሰላሳ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሶስት ብር ከሀያ ሳንቲም /
  2. የፕላንትና ማሽነሪ ጥገና አገልግሎት 6243 ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)
  3. የጉልበት እና ጭነት አገልግሎት 6255 ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  4. ለትራንስፖርት 6232 ብር 12,600.00 (አስራ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ብር)
  5. ህትመት 6213 ብር 4,000.00(አራት ሺህ ብር)
  6. የግቢው ውስጥ ጥገና 6244 ብር 1,050,000.00 (አንድ ሚሊዮን ሀምሳ ሺህ ብር)

በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒዮ ብቻ በማስያዝ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችልና የዘመኑን ግብር የከፈለ
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡ ወይም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  4. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ መ/ፋ/ግ/ን/አ/ደ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በሎት ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  5. ሰነዱ ትራንስፖርትንና ቫትን ያካተተ ሰነድ መቅረብ አለበት
  6. ድርጅቱ ከሚገዛው ዕቃ ላይ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
  7. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% በባንክ በተረጋገጠ /በሲፒኦ / ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በወሰዱት የጨረታ ሠነድ ላይ በመሙላት የግዥውን ዓይነት በታሸገ ኤንቨሎፕ ጀርባ ላይ በመፃፍ ዋናና ኮፒውን የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ ሥራ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ለሚያቀርቡት ዕቃ ፖስታውን ሲያስገቡ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11 ሠዓት ላይ ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሠአት ት/ቤቱ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  11. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

መድኃኔዓለም አጠ/2ኛ/ደረጃ ት/ቤት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታ ከፍ ብሎ ከቶታል ፊት ስፌት ይገኛል ስልክ 0112595594

በጉለሌ ክ/ከ/የመድኃኔዓለም አጠቃላይ

2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-08-13 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11 ሠዓት ላይ ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሠአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 ብር በሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T08:03:14.000Z
← Back to all tenders