Building and equipment maintenance

የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት የትራንስፖርት፣ የህትመት እና የኤሌክትሮኒክስ እቃ ጥገናዎችን በአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የአገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2019

የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዘር የትራንስፖርት የህትመት እና የኤሌክትሮኒክስ እቃ ጥገናዎችን በአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1 የትራንስፖርት
  • ሎት2 የህትመት እና
  • ሎት3 የኤሌክትሮኒክስ እቃ ጥገናዎችን በአገልግሎት ግዥ

በግልጽ ጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

  • ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ: የአቅራቢነት ሊስት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የሚወዳደሩት በሚያመረቱት እቃ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እቃ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ (cpo) በማስያዝ ይሆናል። ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እቃ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
  • የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ሎት1 እና ሎት3 አገልግሎቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት ሰነዱን በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል።
  • ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም፤ የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ሎት1 የትራንስፖርት የሚሆን ብር 10,000 (አሥር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ሎት2 የህትመት 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ሎት3 የኤሌክትሮኒክስ የሚሆን ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • የህትመት ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት የአሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25% ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት።
  • መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

አድራሻ፡- ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር፡- 011-123-4369 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-13 09:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ / ቤት
  • Bid bond: 10,000 ብር በእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T08:19:54.000Z
← Back to all tenders