Oromia

በቡኖ በደሌ ዞን የቦረቻ የወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልላዊ የመንግሥት ግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 ዓ.ም መሰረት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቡኖ በደሌ ዞን የቦረቻ የወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልላዊ የመንግሥት ግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 ዓ.ም መሰረት

1. የተለያዩ ብትን ጨርቃጨርቆችና የተዘጋጁየደንብ አልባሳት

2. እስቴሽነሪና አላቂ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች

3. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪዎች

4 ቋሚ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/

5. የተለያዩ የመኪናና ሞተር ሳይከል ጎማና ካላማዳርያ

6. የተለያዩ የህትመት ስራዎች

7. የተለያዩ የሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ለእዚሁም የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ፦

1. ከላይ የተዘረዘሩ የግዥ አይነቶች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያደሱ፣

3. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 20,000/ሃያ ሺህ/ ማስያዝ የሚችሉ፣

4. VAT No. ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣

5. TIN No ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣

6. በአቅቢነት ዝርዝር መዝገብ ላይ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ናሙና ማቅረብ የሚችሉ፣

7. ተወዳድሮ ያሸነፈውን ዕቃ ሁሉ እስከ ቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፣

8. የተጠቀሱትን ዕቃዎች ሁሉ ኦርጅናል የሆነ ማቅረብ የሚችልና ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ነጋዴ ይህ ማስታወቂያ ወጥቶ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት መሀከል ቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በማኛውም የመንግሥት የስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ዕቃ እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በማስገባት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ

  • ይህ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀን ውስጥ የሚሸጥ በብር 500.00/100/አምስት መቶ ብር ብቻ/ የማይመለስ የሚሸጥና በዚሁ በተጠቀሰው ቀን መሀል ተሞልቶ የሚመለስ መሆኑን እየገለፅን በቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት 16ኛ /አስራ ስድስተኛ/ የስራ ቀን ላይ ቢሮ ቁጥር 6 /ስድስት/ ውስጥ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  • በቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  • ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ትክክለኛ ማስረጃ ስለመሆኑ የሚገልጽ ኦርጅናልና ኮፒው ለየብቻ ከታሸጉ በኋላ በአንድ ፖስታ ታሽጎ መገኘት አለበት።
  • መስሪያ ቤቱ በቂ ምክንያት ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
  • በስልክ ቁጥር 0945 020 246 ደውለው መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡

በቡኖ በደሌ ዞን የቦረቻ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ወጥቶ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-08-19 09:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀን ቆይቶ በ16ኛ /አስራ ስድስተኛ/ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Buno Bedele Borecha Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 01, 2026)
  • Posted at: 2026-08-01T08:43:31.000Z
← Back to all tenders