Garage and vehicle maintenance
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ጋራዦች የተሽከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የመኪና ጥገና ግልጽ የጨረታ
ማስታወቂያ 02/2019
በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ጋራዦች የተሽከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል።
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባቢነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 15ኛው ቀን 11፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብ/አሰ/ዳይሬክቶሬት ይከፈታል። 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 30,000.00 በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የፋይናንሻል፤ የቴክኒክ ሰነድ እነ የሲ.ፒ.ኦ ፖስታ ተለይቶ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት ለ60 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ 05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያዝ በ15 ቀናት ውስጥ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-180-5071 በመደወል ማብራሪያ
መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-18 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Southern Ethiopia Regional State Finance Bureau
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T10:19:17.000Z