Disposal, scrap and surplus sales
ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ያገለገሉ ንብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በክፍት ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- የተለያዩ ያገለገሉ ማሽኖች ማለትም ዶዘር፣ ካሪየር ትራክ፣ ዳምፕ ትራክ፣ የውሃ ማመላለሻ ትራክ፣ ኮንክሪት ማቀላቀያ ትራክ፣ መካከለኛ ጭነት ትራክ፣ ዊል ሎደር፣ ማባይል ክሬን፣
- ያገለገሉ ቫይብሬተሮች፣ ያገለገሉ የውሃ ፓምፖች፣ ያገለገለ ፕሌት ኮምፓክተር፣ ያገለገሉ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች ፣ ፎቶኮፒ ማሽኖች፣ ስካነሮች፣ መጠረዣ/ባይንዲንግ ማሽኖች፣ ፋክስ ማሽኖች፣ ዩፒኤስ (UPS) እና ካልኩሌተሮች፣ ስካውት ሚክሰር፣ ቋሚ ኮንክሪት መቀላቀያ፣ ሚኒ ሮለር፣ ባህላዊ የማቅለጫ መሳሪያ፣ አትላስ ኮፕኮ አየር መጭመቂያ፣ ተንቀሳቃሽ አየር መጭመቂያ፣ የብየዳ ጀነሬተር፣ ሚክሰር ድራም፣ የሚክሰር ትራክ ድራም
- ያገለገሉና አዲስ የተሽከርካሪ እና የማሽነሪ መለዋወጫ እቃዎች፣ ያገለገለሉ አሮጌ ፊልትሮዎች፣ ኤር ክሊነሮች፣ የቫይብሬተርና የተለያዩ ሆዞች፣
- አሮጌ ብረታ ብርቶች፣ ሮለር፣ ቼይን እና የመኪና ቦዲ እቃዎች፣ አሮጌ ቁርጭራጭ ስቶን ከተር ቆርቆሮች፣ አሮጌ ባሌስትሪዎች፣ ቁርጥራጭ አልሙኒየም፣ ፓኔሎች፣ ኤች ፍሬሞች ቁርጥራጭ የአርማታ ብረቶች፣
- ያገለገሉ አሮጌ የተለያዩ ጐማዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ባትሪዎች፣ የተቃጠለ ዘይት ከነበርሜሉ፣ አሮጌ የዘይ ጀሪካን፣ ባዶ የዘይት በርሜል፣ ባዶ የቀለም ቆርቆሮ፣ አሮጌ ቶነሮች፣ የማገዶ እንጨት እና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ በግልጽ ጨረታ አቅርበናል።
ስለዚህ ተጫራቶች የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በዋናው መ/ቤት 3ተኛ ፎቅ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ እና በድርጅቱ ገላን ተርሚናል /ሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ/ በመቅረብ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ንብረቶቹን በአካል ለማየት የጨረታ ሠነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ከሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ዘወትር በሥራ ሰዓት የድርጅቱ ገላን ተርሚናል /በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ፤ እና ዱከም የድርጅቱ ግብዓቶች ማምረቻ ጊቢ (ቢሾፍቱ ከተማ ዱከም ክፍለ ከተማ ኦዳ ነቢ ወረዳ) በመገኘት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።
ጨረታው ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ገላን ተርሚናል ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ዋናው መ/ቤት አድራሻ
ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ቦሌ ፍላሚንጐ ሆቴል ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 011-551 3289 ወይም 011-551 4060
አዲስ አበባ
ገላን ተርሚናል አድራሻ
ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ከአ.አ ዋናው መ/ቤት 27 ኪ.ሜትር ላይ
ሸገር ክፍለ ከተማ፤ ገላን ወረዳ የሚገኘው
የሰንሻይን ገላን ተርሚናል
ስልክ ቁጥር 011-445 0087 እና 011 445 0055/56 በGoogle map መጠቀም ለሚፈልግ
https://maps.app.goo.gl/zQuZuhqquE7jWgNj9
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 13:00
- Bid closing (note): ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም.
- Bid opening: 2026-08-17 13:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Sunshine Construction PLC
- Bid document price: 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር)
- Published on: Reporter (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T12:43:09.000Z