Addis Ababa
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግል ማኅበር የተለያዩ ያገለገሉ የአነስተኛ እና የከባድ መኪኖች እንዲሁም የትራክተር እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች እና ባትሪዎች እንዲሁም ከመነዳሪ እና ፍላፕ በቦንጋ በሚገኘው የውሽውሽ ሻይ ልማት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ
ማስታወቂያ
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ/የተ/የግል ማኅበር የተለያዩ ያገለገሉ የአነስተኛ እና የከባድ መኪኖች እንዲሁም የትራክተር እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች እና ባትሪዎች እንዲሁም ከመነዳሪ እና ፍላፕ በቦንጋ በሚገኘው የውሽውሽ ሻይ ልማት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ህጋዊ የ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ተጫራች በዋናው መ/ቤት የተዘጋጀውን ዝርዝር መረጃውን የያዘ ሰነድ በመግዛት መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ለቀረበው ንብረት በተናጠል ወይም በጥቅል ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታው ነሀሴ 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ሠነድ ማስገባት ያለባቸው በዋና መ/ቤት ብቻ ነው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺኅ) በኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ/የተ/የግ/ ማኅበር ስም የተዘጋጀ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ ወይም “CPO” ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው የንብረቱን አጠቃላይ ዋጋ በቅድሚያ በመክፈል በ30 ቀናት ውስጥ ንብረቱን አጠቃሎ ማንሳት ይኖርበታል።
- ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮች አሸናፊ ተጫራች ከድርጅቱ ጋር በሚፈፅመው ውል ላይ የሚሸፈኑ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በዋና መ/ቤት መግዛት ይቻላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ/የተ/የግል ማኅበር ዋ/ጽ/ ቤት አዲስ አበባ ላም ላሜዴይሪ የሚገኝበት ግቢ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ገበያ እና ሽያጭ መምሪያ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 09 12 50 69 29/ 09 13 42 70 08 ዋናው መ/ቤት እንዲሁም ውሽውሽ ሻይ ልማት 09 35 10 91 79 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኢትዮ አግሪሴፍት ኃ/የተ/የግል ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-13
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-13 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Agri-CEFT Pvt.Ltd.Co.
- Bid bond: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T14:11:39.000Z