Uniforms and workwear
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያዎችን ከአቅራቢዎች በማጫረት መግዛት ይፈልጋል
Description
የደንብ ልብስ ጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያዎችን ከአቅራቢዎች በማጫረት መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ፡-
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑ፣
- የደንብ ልብሶችን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው መሰረት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆኑ በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀጥሎ ባለው ቀን ጀምሮ አምባሰል ህንፃ ቢሮ ቁጥር 503 ቀርባችሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታወጀበት ከ26/11/2018 ዓ.ም ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ ለ22 ተከታታይ ቀናት ብቻ ሲሆን በ22ኛው ቀን በ18/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን በ19/12/2018 ዓ.ም በ4፡00 አ/አበባ የገዥ ዋና መ/ቤት ማለትም አምባሰል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግ. ማህበር
ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንፃ ቢሮ ቁጥር 505/404 ወይም
በስልክ ቁጥር 011 466 6668/ 011 470 0349 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃ.የተ. የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 16:00
- Bid opening: 2026-08-25 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Reporter (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T15:37:58.000Z