Industrial machinery and installation

በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሽገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለፈርኒቸር ሥራ የሚያገለግል የቪነር መለጠፊያ ማሽን (Edge Banding Machine) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የቪኔር መለጠፊያ ግዥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 003/2018/19

ድርጅታችን ለፈርኒቸር ሥራ የሚያገለግል የቪነር መለጠፊያ ማሽን (Edge Banding Machine) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው።

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።

2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) እና የሥራ መለያ ቁጥር ቲን ቁጥር ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾቹ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመኖራቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. ተጫራቾች የቪነር መለጠፍያ ማሽን (Edge Banding Machine) በተጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች ጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።

6. አሸናፊው ተጫራች ስለ ማሽኑ አጠቃቀም ሥልጠና የመስጠትና የመትከል ግዴታ አለበት።

7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ በድርጅቱ ስም ማስያዝ ይኖርበታል።

የጨረታ ሠነዱን ለቡ መብራት ኃይል ሮያል ከረሜላና ቸኮሌት ፋብሪካ ሕንፃ 3ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0979238270/0912080221 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሽገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-18 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T06:49:50.000Z
← Back to all tenders