Uniforms and workwear

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የተለያዩ የሥራ አልባሳት፣ የድርጅቱ ዓርማ የሚታተምበት መለዮና ከረባት እና የተለያዩ ጫማዎች (የሥራና የሴፍቲ ጫማዎች) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2019

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሥራ ትጥቆች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

  • ምድብ 1. የተለያዩ የሥራ አልባሳት
  • ምድብ 2. የድርጅቱ ዓርማ የሚታተምበት መለዮና ከረባት
  • ምድብ 3. የተለያዩ ጫማዎች (የሥራና የሴፍቲ ጫማዎች)

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN No. ) ያላቸው።
  2. የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
  3.  በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች ለምድብ 1፡ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 2፡ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር )፣ እና ለምድብ 3፡ ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪ ዋስትና ( Bid Bond ) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ 25/12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በዚሁ ቀን 25/12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች ለሶስቱም ምድብ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

ስልክ ቁጥር 0115525405/011-551-32 88

ፖ.ሣ.ቁ.3375 አ.አ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-31 10:05
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Petroleum Supply Enterprise
  • Buyer address: ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ ስልክ ቁጥር 011-551-3288 ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T07:26:17.000Z
← Back to all tenders