Garage and vehicle maintenance

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለ2019 ዓ.ም. በጀት ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ጋራዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በውል ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለ2019 ዓ.ም. በጀት ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ጋራዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በውል ለማሰራት ይፈልጋል፤

ስለዚህ መስፈርቱን በማማላት በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፤

1. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚውልና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበትን 20,000.00/ ሃያ ሺ ብር/ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋለ፡፡

4. በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡

5. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. የጨረታ ሰነድ ሃምሌ 22/2018 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 6 /2018 ዓ.ም. ከ11፡00 ሰዓት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተደረር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም. / ከጠዋቱ 3.00 ሣጥኑ ታሽጎ 3.30 ሠዓት ይከፈታል።

8. ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55 / 0251-11-37-43 በመደወል መረጃ ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 ማግኘት ይችላሉ፡፡

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-13
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-08-13 09:30
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Melekite Dire (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T08:00:54.000Z
← Back to all tenders