Garage and vehicle maintenance
በአብክመ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት የመኪና አመታዊ ጥገና፣ የቢሮ ጽዳት አዉት ሶርስ እና ደንብ ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር1/2019
በአብክመ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት ሎት 1. የመኪና አመታዊ ጥገና ፣ ሎት 2. የቢሮ ጽዳት አዉት ሶርስ፣ ሎት 3. ደንብ ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 33 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሁለት በመቶ (ቢድ ቦንድ) በጨረታ ሠነዱ የተገለፀውን የብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤ በተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው። ጨረታዉ በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ፋይ/ንብ/ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዚያዉ ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው።
9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 1068 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 2030 ወይም 058 220 1081 መደወል ይቻላሉ።
የአብክመ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
- Bid opening: 2026-08-18 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Region Administration Bureau
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T08:05:19.000Z