Garage and vehicle maintenance

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለቢሮው እንዲሁም በፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለአብክመ ጣና ሴክሬታሪያት እና ለአብክመ ፖሊሲ ጥናት ኢንስትቲዩት የ2019 በጀት ዓመት የተሽከርካሪ የመድህን ዋስትና አገልግሎት፣ የተሽከርካሪ የጥገና አገልግሎት፣ የቢሮ ጽዳት አውት ሶርስ አገልግሎት፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት እና የፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለቢሮው እንዲሁም በፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለአብክመ ጣና ሴክሬታሪያት እና ለአብክመ ፖሊሲ ጥናት ኢንስትቲዩት የ2019 በጀት ዓመት የተሸከርካሪ የመድህን ዋስትና አገልግሎት፣ የተሸከርካሪ የጥገና አገልግሎት፣ የቢሮ ጽዳት አውት ሶርስ አገልግሎት፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት እና የፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

1. በዘርፉ አግባብነት ያለው እና የታደሰ ህጋዊ  የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የአገልግሎት ግዥዎችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት  ቢሮ ቁጥር 310 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች ለተሸከርካሪ የጥገና አገልግሎት በደረጃ 2 እና በደረጃ 3 ብር 4,000፣ ለደረጃ 3 ብር 5,000 እንዲሁም ለሌሎቹ የአገልግሎት አይነቶች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ (ANRS Plan and Development Bureau) በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሃሴ 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 001 ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00  ይታሸግና በዚሁ ቀን 4፡30  ይከፈታል፡፡

10. አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ለተሸከርካሪ የጥገና አገልግሎት ለእጅ ዋጋ እና የኪሎ ሜትር ዋስትና ድምር ከፍተኛ ነጥብ ያገኘ ሲሆን ለሌሎች አገልገሎቶች በጠቅላላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-18 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Plan and Development Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T08:08:24.000Z
← Back to all tenders