Solar and renewable energy systems
በምዕ/ጎጃም ዞን በፍ/ሠላም ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኘው የጃቢ ህብረት ሥራ ማህበር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ኃ.የተወ. ለቢሮ አገልግሎት የሚውል 6 kw G - POWER በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕ/ጎጃም ዞን በፍ/ሠላም ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኘው የጃቢ ህብረት ሥራ ማህበር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ኃ.የተወ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል 6 kw G - POWER በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች እንድትሣተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- በሌላ ተወዳደሪ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም ::
- ተጫራቾች ለባትሪው 5 ዓመት ለኢንቨንተሪ 2 ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የአንድ ዓመት የጥገና አገልግሎት መሰጠት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የትራንሰፖርት እና ሙሉ የገጠማ ስራ መስራት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለሰ 500 ብር በመክፈል አለባቸው፡፡ ሰነዱን ከድርጀቱ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ ሁለት በመቶ ማሰያዝ ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋና ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ በታሸገ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን በ11ኛው ቀን የሰራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሰራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሸጎ ከጠዋቱ 4፡00 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተገለጡ ሀሳቦች ካሉ በግዥ እና ሸያጭ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ዩኒየኑ ባዘጋጀው ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 1474 /09 10 19 74 55 መደወል ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ፍ/ሠላም ወደ ገበያው መታጠፊያ መንገድ 50 ሜትር ገባ ብሎ
የጃቢ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን
Tender details
- Deadline: 2026-08-13
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00
- Bid opening: 2026-08-13 10:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Jabi Cooperative Work Association Finance Saving and Credit Union Private Limited
- Buyer address: ፍ/ሠላም ወደ ገበያው መታጠፊያ መንገድ 50 ሜትር ገባ ብሎ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T08:37:55.000Z