Oromia
የቱሉቦሎ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሥልጠና የሚውሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን፣ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጸጉርና ውበት ዕቃዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ብትን የደንብ ልብሶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የግንባታ መሳሪያዎችን፣ የልብስ ስፌት ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎችን፣ የፈርኒቸር፣ መለዋወጫ ዕቃዎችን፣ የመካኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019
የቱሉቦሎ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሥልጠና የሚውሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን፣ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጸጉርና ውበት ዕቃዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ብትን የደንብ ልብሶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የግንባታ መሳሪያዎችን፣ የልብስ ስፌት ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎችን፣ የፈርኒቸር፣መለዋወጫ ዕቃዎችን፣ የመካኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) የአቅራቢነት ማስረጃ እና VAT ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የዕቃዎችን፣ ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታተይ የስራ ቀናት በደ/ምዕ/ሸዋ በበቾ ወረዳ ቱሉቦሎ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 1 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው ቦታ ይከፈታል፡፡
6. አስራ አንደኛው ቀን ዝግ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
7. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀ ቀን ጀምሮ እስከ 10 ባሉት ቀናቶች በበቾ ወረዳ ቱሉቦሎ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቱሉቦሎ ከተማ ከኤአ 80 ኪሎ ሜትር በጅማ መንገድ ላይ በራሳቸው መጓጓዣ ዕቃዎችን አቅርበው ማስረከብ አለባቸው::
8. አሸናፊው በጨረታው መሰረት ዕቃዎችን በሙሉ ሲያስረክብ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸምለታል::
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡- ስልክ ቁጥር 0113 421 020 / 0113 420 850
Telegram and face book TBTVET COLLEGE
የቱሉቦሎ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ /ቱሉቦሎ
Tender details
- Deadline: 2026-08-14
- Bid closing time: 12:30
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-14 14:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Tulu Bolo TVET College
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T10:35:20.000Z